ከክፍል ሃያ ዘጠኝ የቀጠለ
የዶግማና የቀኖና ጥሰት በኢ/ኦ/
ተ/ ቤተ ክርስቲያን፤ ክፍል ስድስት
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት
ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
ባለፉው ክፍል 29 ጸሁፋችን ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ ያስተላለፉትን
ውግዘትና ማስረጃዎቹን፤እንዲሁም ውግዘቱን ላለመቀበል የሚቀርቡ ምክንያቶችን አስነብበናችሁ ቀጣዩን ክፍል "ከእኛ ምን ይጠበቃል" በሚለው
ሃሳብ እንመለሳለን ብለን እንደነበር ይታወሳል፡፡ይህ የቤት ሥራችን እንደተጠበቀ ሆኖ ለዛሬው ከአባታችን ከአለቃ አያሌው በስማቸው
ከተከፈተው ድረ-ገጽ www.aleqayalewtamiru.info
ላይ ያገኘነውን ለአስራ አንደኛ ዓመት መታሰቢያቸው የቀረበውን ጽሁፍ ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኋል፡፡
ሰምተን ለመጠቀም ያብቃን፡፡