Thursday, May 31, 2012

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8 ክፍል 4


5. ጳጳሳትና ኤጴስ ቆጶሳት፣ የቤተክርስቲያን አለቆች፣ ካህናትና ዲያቆናት የወጣውን ህግ መቃወም ሲገባቸው የጥፋቱ ተባባሪ ሆነዋል፣ ፓትርያርኩ እንደ አምላክ ያመልካቸዋል ለተባለው፡-
ሀ) ዜና ቤተክርስትያን ጋዜጣ 50ኛ አመት ቁርር 150 ገጽ 10 ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አለቆች ካህናትና ሰራተኖች ለዘመን መለወጫ የደስታ መገለጫዎች ውስጥ የተወሰደ፡-‹‹እንዚሁም የታሪከዊቷ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ርዕሰ መንበር ሲሆኑ ዘይፈቅድ እምኔክሙ ይኩንክሙ ሊቀ ይኩንክሙ ላዕከ ባለው መሰረት መንፈሳዎ ስራዎችዎ በካኅናትና ምዕመናን ዘንድ ሰርፀው ለምልመውና አብበው ፍሬ እንዲያስገኙ እንደ ትጉህ ገበሬ ያለ እረፍት በየቅዱሳን መካናት እየተዘዋወሩ ቃለ ምዕዳንና ትህትናን የተላበሰ መመሪያ በመስጠት የሚያደርጉት ሃዋርያዊ ጥረትና መንፈሳ የስራ ሂደት አዲስ በመሆኑን ስራው አዲስ ከሆነ ደግሞ የስራው ባለቤት የሆኑት ቅዱስ አባታችን አዲስ ሐዋርያ ነዎትና ‹‹ልብስዎ ለሐዲስ ብእሲ›› ያለውን ቃለ ሐዋርያ መነሻ በማድረግ ውስጣዊ ህሊናችንን ከንዋመ ሀኬት ለስራ የሚቀሰቅሰውን ቅዱስ አባት በስራ፤ በምግባር፣ በሃይማኖት እንከተለው ለማለት ጥቅሱን ለመነሻነት ተጠቅመንበታል፡፡››
ለ) ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ 50ኛ ዓመት ቁጥር 163 መስከረም 1 ቀን 1990 ዓ.ም ‹‹የአ/አ፤ አድባራት ገዳማት እራሱን ‹‹መርሀ ተወህዶ›› ብሎ የሚጠራውን ፀረ ቤተ ክርስቲያን ቡድን አውገዙ›› በሚለው ርዕስ ስር የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት የሰንበት ት/ቤት አባላት ፤ የየአጥቢያ ቤ/ክ ሰራተኞች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የቀረበ ፅሁፍ ነው፡- ገፅ 10 እና 13