Sunday, March 8, 2015

ስለ ጽዮን ዝም አልልም!!! ኢሳ.62፥1 ክፍል አራት

ካለፈው የቀጠለ
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣
 “ስለጽዮን ዝም አልልም ” በሚለው ርዕስ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ክፍሎች በቅድስት ቤ/ክ ውስጥና በዙሪያዋ የሚከናወነው ንግድ የተወገዘ እንደሆነ የጌታችንን ወንጌል ጠቅሰን ባቀረብነው ጽሁፍ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

በተለይም በሶስተኛው ክፍል፡-
  1. ለንግድ ሥራ በተሰሩት ህንጻዎችና ሱቆች አብያተ ርስቲያናቱ መሸፈናቸውን ፤
  2. ለልማቱ ሲባል በክብር ያረፉ የክርስቲያኖች አጽሞች ከአፈር ጋር እየተፈነቀሉ መጣላቸው
  3. በየንግድ ቤቶቹ ውስጥ አጸያፊና ኢክርስቲያናዊ ነገሮች እየተፈጸሙ መሆናቸውን፤
  4. የንግድ ቤቶቹን የሚከራዩት ከሃይማኖታችን ውጪ የሆኑ ሰዎችም ጭምር መሆናቸው
  5. የእያንዳንዱ ቤርስቲያን የገቢ መጠን መዛባት የሚያመጣውን አሉታዊ ተጽእኖ ፤ወ.ዘ.ተ
ተመልክተን በይቀጥላል አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም በተለያዩ የግል ማህበራዊ ጉዳዮች ምክንያት ለተወሰኑ ጊዜያት ብንዘገይም ለዚህ ጊዜ ያደረሰንን ልዑል እግዚአብሔርን እያመሰገንን ከዚህ ቀጥሎ ‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ከተሰኘው ድረ ገጽ ላይ ያገኘነውን ጽሁፍ እንድታነቡ እንጋብዛለን፡፡ ‹‹ከድጡ ወደ ማጡ›› እንዲሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተልዕኮዋ ውጪ በንግድ ሥራ ላይ መሰማራቷ አነሶ ሀብትና ንብረቷ በማናለብኝና በአሳፋሪ ሁኔታ እየተዘረፈ ለግለሰቦች መጠቀሚያ፤እንዲሁም ደግሞ ለመናፍቃን መጠቋቆሚያ እየሆነች ነው፡፡