Friday, June 15, 2012

“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፩


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ አሜን
“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ክፍል ፩
                                 ማቴ, ፳፬ ቁ, ፬

         በዚህ ጽሑፍ በጥር ወር 1988 ዓ.ም  ”የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፤ሥርዓተ እምልኮትና የውጭ ግንኙነት ”በሚል ስያሜ የተዘጋጀው መጽሐፍ  ”ሦስት መለኮት“ ከሚለው  ጀምሮ በውስጡ የያዘውን ጎላ ጎላ ያለ ስህተትና ይህንኑ መሰረት በማድረግ የተፈጠሩትን ችግሮች የምንመለከት ሲሆን በቅድሚያ ግን ይህንን የክህደት መጽሐፍ ታዘጋጁት እነማን እንደሆኑ እናያለን::

Friday, June 1, 2012

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8 ክፍል 1



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የእውነት ምስክርነት 
“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8
  
           የክርስትና ሃይማኖት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ከአባቶች ወደ ልጆች እየተላለፈ ዛሬ እኛ አለንበት ዘመን ደርሷል፡፡ ወደፊትም እስከ ምጽአት ድረስ ይኖራል፡፡ ይህንኑ በማስመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ አለት እንደሆንክ እኔ እነግርሃለሁ በዚያች አለት ላይም ቤተክርስቲያኔን እሰራታለሁ የሲኦል በሮችም አይበረቱባትም” ማቴ 16፡18) በማለት እንደነገረው ቤተክርስቲያን እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ በአጋንንትና የነሱ ተገዢ በሆኑ መናፍቃንና ከሃድያን እንደምትፈተን ነገር ግን እንደማይበረቱባት ወይም እንደማያሸንፏት ቃል ገብቶላታል፡፡ እንዲህም ስለሆነ ገና በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ከተነሱት ከቢፅ ሃሳውያን ጀምሮ በዋነኞቹ መናፍቃን በነአርዮስ መቅዶንዮስ ስጥሮስ ልዩንና ሉተር ከነተከታዮቻቸው በከሃድያኑ በነዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ በአገራችን በነጉዲትና በነአህመድ ግራኝ ብዙ ተፈትናለች ብዙ ልጆችዋ እምነታችንንና ሥርአታችንን አንለውጥም ብለው ሕይወታቸውን ሰውተዋል በነሱ ሰማእትነት ክርስትና እየተስፋፋ ሄደ እንጂ እንደ ተቃዋሚዎቹ ምኞት ክርስትና ወይንም ቤተክርስቲያን አልጠፋም፡፡
የቀደመው የቤተክርስቲያን ችግር መልክ ነበረው መናፍቃኑ ስለሚያምኑት ነገር በግልጥ ይናገራሉ የቤተክርስቲያን አባቶች በጉባዔ ክርክር ያደርጋሉ መናፍቃኑ ይረታሉ ይወገዛሉ ከሃዲያኑ በበኩላቸው ጣኦት ያቆማሉ ለነሱ የሰገደ ይኖራል አልሰግድም ያለ በሞት ይቀጣል፡፡ የአሁኑ ዘመን ችግር ግን ቤተክርስቲያን ሳይሆኑ ነን በማለት አንዳንድ ሥርዓቶችን ለይምሰል በመፈጸም አመቺ ሁኔታ ሲያገኙ የዋሃን ምእመናንን በተለያ መንገድ እያታለሉ በማስካድ ላይ ናቸው፡፡ ይህ አይነቱ መስሎ የመኖርና የማጭበርበር አካሄድ በተራው ሰው ደረጃ ብቻ ቢደረግ ባላስደነቀም ነበር የሚገርመው ግን የቤተክርስቲያን አባቶች ምእመናንን ከተኩላ ለመጠበቅና ቤተክርስቲያንን ለማስተዳደር ከሰውና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት በመዘንጋት ተገቢ ያልሆነ ሥራ ሲሰሩ ከማየት የበለጠ አሳዛኝና አሳፋሪ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ክፍል 2


3. የኑፋቄ መጽሐፍ አሳትመዋል ለተባለው፡-
1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክረስቲያን እምነትና ሥርዓት አምኮትና የውጭ ግንኙነት የሚለውን መጽሐፍ ያዘጋጁት 6 ጳጳሳትና 11 በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ሲሆኑ መጽሐፉ ግን ብዙ ስህተቶችን ይዟል፡፡ ይህን መጽፍ አለቃ ኤሌው ካወገዙትና ምዕመናንም በሰላማዊ ሰልፍ ከተቃወሙት በኋላ ስህተቶቹ ጥቂቶቹ ብቻ በሚስጥር ታርመው ማለት ለምዕመናን ግልጽ ሳይደረግ በድጋሚ የታተመ ተብሎ ተዘግጅቷል፡፡ የመጀመሪያው ጥር 1988 ዓ.ም የታተመ ሲሆን ሁለተኛው በሐምሌ 1988 ዓ.ም ነው፡፡ ችግሩን ለማሳየት ያህል ዋና ዋናዎቹን አምስት ሀሳቦች ከሁለቱም መፃህፍት በቀጥታ ወስደን ስንመለከታቸው ይህንን ይመስላሉ፡፡
ሀ) “እገዚአብሔር ወልድ ሰው በሆነበት ምክንያት “ በሚለው ርዕስ ስር ከገጽ 17 የመጀመሪያው እትም የተወሰደ “ሰው ሆነ ማለት የሰውን ጠባያት፣ ነፍስንና ስጋን በረቂቅ ባህሪው ተዋህደ ማለት ው:: በዚህም የነቢያት ቃል ሁሉ ተፈጸመ” ከገጽ 26 ሁለተኛው እትም የተወሰደ (የታረመው) ‹‹ሰው ሆነ ማለትም በተለየ አካሉ ነፍስንና ሥጋን ተዋሃደ ማለት ነው በዚህም የነቢያት ቃል ሁሉ ተፈፀመ››

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8 ክፍል 3


4. ፓትርያርኩ የሲኖዶስን ሥልጣን የሚሽርና እራሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ እንዲሰየሙ የሚያደርግ አዲስ ሕግ      አወጡ ለተባለው፤
1. ሚያዚያ 30 ቀን 1988 ዓ.ም ከተዘጋጀው ህገ ቤተ ክርስቲያን
1.1 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 5 የቅዱስ ሲኖዶሱ ሥልጣን ተግባር ተራ ቁ.1 የቅዱስ ሲኖዶሱ በፓትርያርኩ አመራር ሰጪነትና ሰብሳቢነት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡
1.2 ምዕራፍ 5 ቀን አንቀፅ 14 የፓትርያርኩ ከማዕረግ መውረድ ተራ ቁ.2 ‹‹ ፓትርያኩ የተዋህዶ ሃይማኖትን የሚያፋልስ ሕግጋት ቤተ ክርስቲያንን የማይብቅ ማዕረጉን የሚያጎድፍ ሆነ መገኘቱ በተጨባጭ ማስተጃ ሲረጋገጥ በምልአተ ጉበዔ ያለ አንዳች የሃሳብ ልዩነት በቅዱስ ሲኖዶስ ከተጠና በኋላ በቅድስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት ከማዕረጉ ይወርዳል፡፡
1.3 ምዕራፍ 8 አንቀጽ 23 የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ፀሀፊ በሚለው ርዕስ ሥር ተራ ቁ. 3/ለ/ ‹‹የሲኖዶሱ ዋና ፀሀፊ የቅዱስ አባልና ፀሀፊ ሆኖ ተጠቲነቱ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ይሆናል፡፡››
1.4 ምዕራፍ 9 አንቀፅ 25…‹‹ከቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት መካከል በቅ/ፓትርያርኩ አቅራቢነት ሶስት ዕጩዎች ተወዳድረው     በቅ/ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ የተመረጠው የመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በቅዱስ ፓትርያርኩ ይሾማል፡፡
1.5 ምዕራፍ 16 አንቀፅ 33 ‹‹ካሁን በፊት በቅ/ሲኖዶስ ወጥተው የነበሩ ህጎች በዚህ ሕግ ተሻሽለዋል፡፡
·         የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር አደባባይ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ያለው ችግር እንዲያጣራ ህዳር 5 ቀን 1990 ዓ.ም በፓትርያርኩ ሥልጣን የተሰጠው አጣሪ ኮሚሽን አቅሙ የፈቀደውን ያህል ከላይ የተጠቀሰውን ሕግና ሌሎችንም ችግሮች በማጥናት ሁለት ክፍል ያለው ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ከዚህ ውስጥ አዲሱን ህገ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ቀድሞ ከነበሩት ህጎች ጋር እንዲህ ያነፃጽረዋል፡፡