Friday, June 1, 2012

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8 ክፍል 1



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የእውነት ምስክርነት 
“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8
  
           የክርስትና ሃይማኖት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ከአባቶች ወደ ልጆች እየተላለፈ ዛሬ እኛ አለንበት ዘመን ደርሷል፡፡ ወደፊትም እስከ ምጽአት ድረስ ይኖራል፡፡ ይህንኑ በማስመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ “አንተ አለት እንደሆንክ እኔ እነግርሃለሁ በዚያች አለት ላይም ቤተክርስቲያኔን እሰራታለሁ የሲኦል በሮችም አይበረቱባትም” ማቴ 16፡18) በማለት እንደነገረው ቤተክርስቲያን እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ በአጋንንትና የነሱ ተገዢ በሆኑ መናፍቃንና ከሃድያን እንደምትፈተን ነገር ግን እንደማይበረቱባት ወይም እንደማያሸንፏት ቃል ገብቶላታል፡፡ እንዲህም ስለሆነ ገና በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ከተነሱት ከቢፅ ሃሳውያን ጀምሮ በዋነኞቹ መናፍቃን በነአርዮስ መቅዶንዮስ ስጥሮስ ልዩንና ሉተር ከነተከታዮቻቸው በከሃድያኑ በነዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ በአገራችን በነጉዲትና በነአህመድ ግራኝ ብዙ ተፈትናለች ብዙ ልጆችዋ እምነታችንንና ሥርአታችንን አንለውጥም ብለው ሕይወታቸውን ሰውተዋል በነሱ ሰማእትነት ክርስትና እየተስፋፋ ሄደ እንጂ እንደ ተቃዋሚዎቹ ምኞት ክርስትና ወይንም ቤተክርስቲያን አልጠፋም፡፡
የቀደመው የቤተክርስቲያን ችግር መልክ ነበረው መናፍቃኑ ስለሚያምኑት ነገር በግልጥ ይናገራሉ የቤተክርስቲያን አባቶች በጉባዔ ክርክር ያደርጋሉ መናፍቃኑ ይረታሉ ይወገዛሉ ከሃዲያኑ በበኩላቸው ጣኦት ያቆማሉ ለነሱ የሰገደ ይኖራል አልሰግድም ያለ በሞት ይቀጣል፡፡ የአሁኑ ዘመን ችግር ግን ቤተክርስቲያን ሳይሆኑ ነን በማለት አንዳንድ ሥርዓቶችን ለይምሰል በመፈጸም አመቺ ሁኔታ ሲያገኙ የዋሃን ምእመናንን በተለያ መንገድ እያታለሉ በማስካድ ላይ ናቸው፡፡ ይህ አይነቱ መስሎ የመኖርና የማጭበርበር አካሄድ በተራው ሰው ደረጃ ብቻ ቢደረግ ባላስደነቀም ነበር የሚገርመው ግን የቤተክርስቲያን አባቶች ምእመናንን ከተኩላ ለመጠበቅና ቤተክርስቲያንን ለማስተዳደር ከሰውና ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት በመዘንጋት ተገቢ ያልሆነ ሥራ ሲሰሩ ከማየት የበለጠ አሳዛኝና አሳፋሪ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡

   ይህችን አጭር የማገናዘቢያ ጹሁፍ ለማዘጋጀት የተነሳሁበት ዋናው ምክንያት ምንም እንኳን መልካ ምግባር የሌለኝ ደካማ ብሆንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ልጅ እንደመሆኔ ቤተክርስቲያንን የሚመለከቱ ጹሁፎች ማለት ጋዜጦችን መጽሔቶችንና መጻህፍትን አሰባስባለሁ ከላይ እንደገለጽኩት የኢ/ኦ/ተ/ቤ ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ ይህንኑ ችግር በማስመልከት የቀድሞው የሉቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ አለቃ አያሌው ታምሩ ችግሩ ሥር ሳይሰድ ገና ከጅምሩ እንዲታረም ማሳሰቢያና ተማጽኖ ቢያቀርቡም ሰሚ ስልተገኘ ጥፋተኞችንና ተከታዮቻቸውን አውግዘዋል በአንጻሩ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ እምነትና ሥርዓት ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ ከመጥፋት ላይ ይገኛል እኔም ምንም አይነት የወገናዊነት መንፈስ ሳልይዝ በሁለቱም በኩል የሚሰነዘሩትን ዋና ዋና ሃሳቦች ከተጻፉት ጋዜጣና መጽፍ እንዳለ በመውሰድ ያቀረብኩዋቸው ስለሆነ ማንኛውም አንባቢ እውነቱ የትኛው እንደሆነ በቀላሉ ሊረዳው ይችላል ለጹሁፉ መነሻ ያደረግሁዋቸው ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት አምለኮትና የውጭ ግንኙነት መጽሐፍ ሚያዚያ 30 ቀን 1988 ዓ.ም በሲኖዶስ የተዘጋጀው አዲ ሕገ ቤተክርስቲያን፤ ይህንኑ የቤተክረስቲያን ችግር ለማጣራት የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን ሪፖርት ፣ የነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ብዙ ሲሆኑ ዋናውን ፍሬ ነገር የያዙትን መብሩክ ጋዜጣና ኢትዮ ታይም ጋዜጣ በመጥቀስ ፍሬ ነገሩን እጀምራለሁ፡፡

1.   /  ሰኔ 27 ቀን 1988 ዓ.ም ከወጣው መብሩክ ጋዜጣ ገጽ 6 የተወሰደ
“ይህንንም እንደሚከተለው እገልጣለሁ፡፡”(አለቃ አያሌው ታምሩ)
ሀ.   በቤተክርስቲያን የደረሱ ልዩ ልዩ ችግሮ ሁሉ በሲኖዶስ ተመክሮባቸው እንዲወገና እርምጃቸውም እንዲገታ በ1987 ዓ.ም ጥቅምትና ህዳር ወር ለሲኖዶሱ ማመልከቻ ስጽፍ መልእክቴ በጌታዬ በአምላኬ ትእዛዝ የተደረገ መሆኑን ገለጨ በአፈጻጸሙ ቸልተኝነት እንዳይታይበት ሲኖዶሱን በሾመ በመንፈስ ቅዱስ ዳኝነት ተማጽኜ አቤቱታዬ የእኔ ብቻ ሳይሆን በአጸደ ስጋና በአጸደ ነፍስ ያሉ የኦርቶዶክሳውያን አበውና ምእመናን አቤቱታ መሆኑን ገልጩ ነበር ያቀረብኩት፡፡ ነገር ግን የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አባ ገሪማና ፓትሪያሪኩ ሀሳባቸው እስከ አሁን በቤተ ክርስቲያን የኖረውን የመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሽረው የራሳቸውን ጣዖታዊ መሪነት ለመተካት ኖሮ በጥቅምት 1988 ዓ.ም አጠቃላይ ጉባዔ ላይ ያቀረብኩትን አቤቱታ ጭምር ሳይቀበሉ ከመቅረታቸውም በላይ የመንፈስ ቅዱስን ዳኝነት የሲኖዶሱን ሥልጣን ለግል አድመኞቻቸው ኮሚቴ አሳልፈው በመስጠትና በነሱ ውሳኔ ተደግፈው የኑፋቄ መጽሐፍ ማውጣታቸውና መበተናቸው አንሶ ኦርቶዶክሳዊውን የሊቃውንት ጉባዔ አፍርሰዋል፡፡
2.  ይህ በዚህ እንዳለ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ ጉዳዩን እንዲያይ በግል ማመልከቻ በነፃ ፕሬሱ በኩልም ተቃውሞዬን በማሰማት ላይ እያለሁ ሚያዚያ 18 ቀን 1988 ዓ.ም ቅሬታ አስወጋጅ በሚሉት የግል ኮሚቴያቸው ድጋፍ እኔን ካባረሩ በኋላ ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት 6 ባደረጉት በአፈና የሲኖዶስ ስሰባ ሕግ አስወጥተው በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ ራሳቸው ፓትሪያሪኩ ሲኖዶሱ ወንጌልን ለሚሰብክበት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ለሚያስተምርበት ጉዞ አመራር ሰጪ /ጣኦት/ ወደ መሆን አድገዋል በቤተ ክርስቲያን ስም ተሰይመው እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን ሊያገለግሉ የተሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ሳይቀር ለቤተክርስቲያን ተጠሪ መሆናቸው ቀርቶ ለፓትሪያሪኩ ተጠሪዎች እንዲሆኑ ሲያደርጉ ሚያዚያ 30 ቀን ተፈርሞ ጸድቋል፡፡የተባለውና በጽ/ቤቱ አማካኝነት ለሚመለከተው ሁሉ እንዲተላለፍ በቃለ ጉባዔ ትእዛዝ የተሰጠበት ሕገ ቤተክርስቲያን እስከ አሁን ቤ/ክ ስትሰራባቸው የኖሩት ሕጎችና ደንቦ ሁሉ በዚህ ሕግ ተሻሽለው ከስፍራቸው ሲወገዱ ብጹእ አቡነ ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ የቤተ ክርስቲያኒቱን የአመራር ሰጪነት ቦታ ሲይዙ በቤተ ክርስቲን ላይ የአምልኮ ጣኦት አዋጅ አውጀውባታል ፓትሪያሪኩ በሾማአቸው በእግዚአብሔርና በቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ተግባር ታላቅ በደል ፈጽዋል፡፤ ከራሳቸው ጋር ቃላቸውን ለማጽቅ ምኞታቸውን ለሟሟላት በሕጉ ላይ ፈርመዋል ተብሎ ስማቸው የተመዘገበላቸው 34ቱ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት እንደተባለው አድርገውት ከሆነ ለፈጸሙት በደል ተባባሪዎች ናቸው፡፡
ይህም እጅግ የሚያሳዝን ነው የሚገርመው ደግሞ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 14 “ፓትሪያሪኩ” የተዋህዶ እምነትን ሕግጋት ቤተክርስቲያንን የማይጠብቅ ማእረጉን የሚያጉድፍ ሆኖ በመገኘቱ በተጨባጭ ማስረጃ ሲረጋገጥ በምልዓተ ጉባዔ ያለአንዳች የሃሳብ ልዩነት በቅዱስ ሲኖዶስ ከተጠና በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት ከማዕረጉ ይወርዳል” የሚል ቃል አስፍሮ ሲኖዶሱን በአፈና ል ስልጣን ተጠቅሞና እንደሌለ አድርገው ካሳዩ በኋላ የኑፋቄ መጻህፍት በማሳተም የተዋህዶ ሃይማኖትን አፍልሰዋል ሕገ ቤተክርስቲንን ሳይጠብቁ ቤተክርስቲያን ከምታወግዛቸው ጋር የጸሎት ቅዳሴና የማዕድ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ከምታወግዘው ፓፓ ቡራኬ ተቀብለዋል እያልን እየተቃወምን ለተቃውሟችንንም ተጨባጭ ማስረጃ እያቀረብን እራሳቸውም ይህንን ሳይቃወሙ ይህ እንዳይቀጥል በስልጣናቸው ተጠቅመው ኦርቶዶክሳዊውን የሊቃውንት ጉባዔ ሲያፈርሱ ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ በመስጠት ፈንታ እንደገና በሕግ በመንፈስ ቅዱስ ሥፍራ ተተክተው ለሲኖዶሱ ስልጣንና ተግባር አመራር ሰጪ ይሆናሉ፡፡ የሲኖዶሱ አባሎች ሁሉ ለፓትሪያሪኩ ተጠሪ ይሆናሉ ሲል የወጣው አዋጅ አፈፃፀም ነው፡፡
ይህ ሕገ ቤተክርስቲያን ተብሎ የታወጀው ህግ -- “እስመ ሜጥዋ ለአመፃ ላእሌከ…” አመጽን ወዳንተ መለሳት /ተብሎ እንደተፃፈ ቤተክርስቲያንን መካነ ጣዖት ምእመናንን መምለኪያ ጣዖት የሚያሰኝ ስለሆነ በሙሉ ድምጽ እንድትቃወሙት በእግዚአብሔርና በቤተ ክረስቲያን ስም እጠይቃለሁ፡፡
3.  ከአሁን ጀምሮ ማለት ይህ ቃል በነፃው ፕሬስ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቃልና እጅ በሲኖዶሱ ጸሐፊ በአቡነ ገሪማ ቃልና እጅ ይህን የተፃፈውን ሕግ የቤተክርስቲን ሕግ ብለው አጽድቀው በተባባሪነት አሳልፈዋል የተበለ ጳጳሳትና ሁሉ እውነት ሆኖ ከተገኘ የነሱ ተባባሪዎች ናቸውና በነሱ ቃልና እጅ ቡራኬ እንዳትቀበሉ እንዳትዘዙ ስማቸውን በጸሎት ቅዳሴ የሚጠሩ አለቆች ቀሳስት ካህናት ካሉም አምልኮ ጣኦት አራማጅ ናቸውና ተጠንቀቁባቸው ምክር ስጡአቸው እምቢ ካሉም ተለዩዋቸው፡፡
እንዲሁም ሀምሌ 5 ወይም 6 ቀን ይከበራል ተብሎ ሽርጉድ የሚባልለት በዓለ ሲመት የአሮን የወርቅ ጥጃ መታሰቢያ ሆኖ በቤተክረስቲያን ሊከበር የማገባው ስለሆነ በዓሉ ከመድረሱ በፊት የሲኖዶሱ አባላት በአስቸኳይ ተሰብስበው ሕጉን ካልሻሩና በጣኦትነት የተሰየሙትን አቡነ ጳውሎስን ከስልጣናቸው ካላነሱ ይህንን እንዳታከብሩ ለቤተክርስቲያን ደሙን ባፈሰሰ አምላክ ስም ቤተክርስቲያን በሚመራ በሚጠብቅ በመፈስ ቅዱስ ስም ጥያቄዬን አስተላልፋለሁ፡፡
ምናልባት የሕጉን ጹሁፍ አንብቦ መረዳት የተሳነው ግን በልዩ ልዩ ደጋፊዎቻቸው ተጭበርብሮ በቸልታ የሚመለከተው ከዚያም አልፎ በስልጣናቸው እየተመኩ ለቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ጆሮአችንን አንሰጥም ብለው ይህን በደል ያደረሱትን ፓትሪያሪክ አቡነ ጳውሎስን በ3 የሹመት ስም የሚንቀባረሩትን አባ ገሪማን ለነሱ ድጋፍ የሚሰጡትንም ሁሉ ጌታዬ አምላኬ በምድር ያሰራችሁትን በሰማይ የታሰረ ይሆናል ሲል በሰጠው ቃል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስልጣን በጥሮስ ፣ በጳውሎስ፣ በማርቆስ፣በቄሎስ፣ በባስልዮስ፣ በቴዎፍሎስ፣ በተክለ ሐይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ቃ፤ ሃጥእ ደካማም በምሆን በእኔም በቀሲስ  ወልደ ጊዮርጊስ ቃል አወግዛለሁ፡፡
       ይህን ሕግ የተቀበሉ ከሥራ ላይ ያዋሉ ሁሉ እንደ አርዮስ እንደ መቅዶንዩስ እንደ ንስጥሮስ እንደ ፍላብያኖስ እንደ ኬልቄዶን ጉባዔና ተከታዮቹ እሱራን ውጉዛን ይሁኑ በማይፈታው በእግዚአብሔር ሥልጣን አስሬአለሁ፡፡
                       ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን አሜን፡፡
ማስጠንቀቂያ
አምላኬ ሂድ ተናገር ያለኝን ትዕዛዝ ለናንተ አድርሻለሁ ሩጫን ጨርሻለሁ ከእንግዲህ ተጠያቂነቱ የእናንተ የምእመናንና ታሪክ ተጠያቂ ያደረገው የመንግስት ነው ለዚህም ምስክሬ እራሱ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላዕክት ሰማይና ምድር ናቸው፡፡››
                                                                             አለቃ አያሌው ታምሩ
                                                                             ዘዲማ ጊዮርጊስ
       ሐምሌ 12 ቀን 1991 ዓ.ም በወጣው ኢትዮ ታይም ጋዜጣ ላይ አለቃ አያሌው ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ችግሮች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ. ፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስ የኑፋቄ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡
ለ. ፓትሪያሪኩ የሲኖዶሱን ስልጣን ለራሳቸው የሚያደርግ አዲስ ሕግ አውጥተው እስከ ሚያዚያ 30/1988 ዓ.ም ድረስ የነበሩትን ሕጎች ሽረው በዚህ መሰረት በመንፈስ ቅዱስ ቦታ ተተክተው በቤተክርስቲያን ላይ የጣዖት አምልኮ አውጀውበታል፡፡
ሐ. ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት አለቆች ካህናትና ዲያቆናትም የወጣውን አዲስ ሕግ መቃወም ሲገባቸው የጥፋቱ ተባባሪዎች ሆነዋል፡፡
መ.ፓትሪያሪኩ በተሸሙ በአመታቸው በ1985 ዓ.ም ሮም ሄደው ከፓፓው ጋር የጸሎት፣ የቅዳሴ፣ የመብልና የመሳሰሉትን ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
ሠ.በ1986 ዓ.ም ግሪክ (አቴንስ) ሄደው በሮም እንዳደረጉት ተመሳሳይ ሥርዓት ፈጽመዋል፡፡
ረ. በ1987 ዓ.ም አሲሲ ሮም ሄደው ከሮማው ፓፓ ጋር ስብሰባ አድርገዋል፡፡
ሰ. ፓትርያሪኩ የፕሮቴስታንት ምሩቅ ስለሆኑ የነሱን ዓላማ እያስፈጸሙ ነው፡፡
ሸ. ከእስላም፣ ከካቶሊክ ከፕሮቴስታንት ጋር በመተባበር ሁሉንም የሃይማኖት አባቶች ናቸው በማለት በአገሪቱ ላይ 4 ዓይነት እምነት አውጀውባታል፡፡
ቀ. ጥር 1 ቀን 1989 ዓ.ም በቅ/እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት በታቦት ፊት ሰው አስገድለዋል፡፡
በ. ጥር 4 ቀን 1989 ዓ.ም በቅዱስ ዩሐንስ ቤተክርስቲያን ብዙ ምዕመናንን በፖሊስ አስደብድበዋል፡፡
ተ. አስራ ስድስት ጳጳሳትን በሰኞ ቀን ሐምሌ 5 1991 ዓ.ም በቀይ ልብስ ሾመዋል፡፡ ማለት ሹመቱም በእለተ እሁድ መደረግ ሲገባው በዘፈቀደ መሾና ቀይ ለብስ የካቶሊክ ስለሆነ ኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ነቅለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተክለዋል፡፤ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ችግሮች እስከ 1991 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የነበሩት ሲሆኑ አለቃ አያሌው የጠቀሷቸው ችግሮች እውነት ናቸው ሀሰት ለሚለው የሚከተሉትን እንመልከት፡፡


    
   

No comments:

Post a Comment