Friday, June 1, 2012

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ክፍል 2


3. የኑፋቄ መጽሐፍ አሳትመዋል ለተባለው፡-
1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክረስቲያን እምነትና ሥርዓት አምኮትና የውጭ ግንኙነት የሚለውን መጽሐፍ ያዘጋጁት 6 ጳጳሳትና 11 በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ሲሆኑ መጽሐፉ ግን ብዙ ስህተቶችን ይዟል፡፡ ይህን መጽፍ አለቃ ኤሌው ካወገዙትና ምዕመናንም በሰላማዊ ሰልፍ ከተቃወሙት በኋላ ስህተቶቹ ጥቂቶቹ ብቻ በሚስጥር ታርመው ማለት ለምዕመናን ግልጽ ሳይደረግ በድጋሚ የታተመ ተብሎ ተዘግጅቷል፡፡ የመጀመሪያው ጥር 1988 ዓ.ም የታተመ ሲሆን ሁለተኛው በሐምሌ 1988 ዓ.ም ነው፡፡ ችግሩን ለማሳየት ያህል ዋና ዋናዎቹን አምስት ሀሳቦች ከሁለቱም መፃህፍት በቀጥታ ወስደን ስንመለከታቸው ይህንን ይመስላሉ፡፡
ሀ) “እገዚአብሔር ወልድ ሰው በሆነበት ምክንያት “ በሚለው ርዕስ ስር ከገጽ 17 የመጀመሪያው እትም የተወሰደ “ሰው ሆነ ማለት የሰውን ጠባያት፣ ነፍስንና ስጋን በረቂቅ ባህሪው ተዋህደ ማለት ው:: በዚህም የነቢያት ቃል ሁሉ ተፈጸመ” ከገጽ 26 ሁለተኛው እትም የተወሰደ (የታረመው) ‹‹ሰው ሆነ ማለትም በተለየ አካሉ ነፍስንና ሥጋን ተዋሃደ ማለት ነው በዚህም የነቢያት ቃል ሁሉ ተፈፀመ››


ለ) “ክብረ ቅድስት ድንግለ ማርያም” በሚለው ርዕስ ስር ከገጽ 37 የመጀመሪያው እትም “እመቤታችን በዘመኗ ከነበሩት ደናግል ተለይታ እግዚአብሔር ከፈጠራት ጀምሮ በሃሳብ ፣ በመናገር፣ በመስራት ፣ ንጹሀ ጠባይዕ ያላደፈባት ድንግል ናት” ገጽ 49 ሁለተኛው ዕትም (የታረመው) “እመቤታችን ከሌሎች ሴቶች ሁሉ ተለይታ እግዚአብሔር ከፈጠራት ጀምሮ በሀሳብ፣በመናገር፣ በመስራት ንፅሀ ጠባይዕ ያላደፈባት ንፅህት ናት”
ሐ) “የአማላጅነት ቃል ኪዳን” በሚል ርእስ ስር ገጽ 39 የመጀመሪያው እትም “ቤተ ክርስቲያን ስለ እመቤታችን አማላጅነት እና ቃል ኪዳን የምታስተምረው ፍጹም በሆነ ሀዋሪያዊ ትውፊቅ ነው፡፤” ገጽ 52 ሁለተኛው ዕትም (የታረመው) “ቤተክርስቲያን  ስለእመቤታችን አማላጅነት እና ቃልኪዳን የምታስተምረው በቅዱስ መጽፍ የተጻፈው እና ፍጹም በሆነ ሀዋርያዊ ትውፊት ነው፡፡”
መ) “mystery of the trinity” በሚል ርዕስ chapter 3 page 15 “when we say they are three in essence, in divinity, in existence and in will do not mean to say three Gods but one God.” Chapter 3 page 25 የታረመው
   “Even though we say the trinty are three in name, in deed and in person, the three are one in essence, in divinity, in existence and in will we do not mean three Gods but one God.”
ሠ) የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የውጭ ግንኙነት በአሁኑ ጊዜ በሚለው ርእስ ስር ምእራፍ 27 የመጀመሪያው መጽሐፍ ገጽ 108 በሁለተኛው መጽፍ ገጽ 135 በዚህ ምእራፍ ላይ በታረመው ሆነ ባልታረመው መጽሐፍ ጽሁፉ አንድ ነው፡፡
        ‹‹ይሁን እንጂ በኦሪየንታል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት በኩል ለልዩነቱ ምክንያት ሆኖ የቆየው ይህ የሚስጥረ ስጋዌ ትምህርት ሆኖ እያለ በምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በኩል ቤተ ክርስቲያን ለሁለት እንድትከፈል ምክንያት የሆነው በቃላት የአገላለጽ ልዩነት እንጂ በሁለቱም በኩል ተዋህዶው መሠረት እምነት አንድ መሆኑ ተጠቅሶ ወደፊት ወደ አንድነት ሊያመጣ የሚችል የጋራ ውይይት መድረክ እንዲከፈት ተደረገ›› ገፅ 109 የመጀመሪያው ገፅ 135 በሁለተኛው ‹‹በጉባዔያቱ ሁሉ የኬልቄዶኑ ውግዘት መነሻ ምክንያቶች በጥልቅ ተመርምረዋል በመጨረሻም በቻምቤዚ ከህዳር 1-6 ቀን 1996 ዓ.ም እ.ኤ.አ በተደረገው ጉባዔ በምስጢረ ሥጋዌ ስለ ክርስቶስ ተዋህዶ የሚሰጠው ትምህርት ልዩነት በሁለቱም ወገኖች የቃላት አገላለጥ እንጂ የእምነት አለመሆኑን ተገንዝበናል፡፡›› ገጽ 110 በመጀመሪያው ገጽ 136 በሁለተኛው ‹‹ ስለዚህም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ከመራራቅ ይልቅ መቀራረብ፤ ከመለያየት ይልቅ በአንድነት መተሳሰብና መረዳዳት ጊዜው የሚጠይቀው መንፈሳዊና ማህበራዊ ግዴታ ከመሆኑም በላይ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የነበረው የምስጢረ ሥጋዌ ትምህርት ልዩነት ከሚወገድበት ደረጃ ላይ እንህ ከተደረሰ በእምነትና በሥርዓጥ ከሚመስሉዋት እህት አብያተ ክርስቲያናት ጋር በአንድነት መከራ ወደፊት በሚደረገው ጉባዔ አንድ አካል ሁለት ባህርይ ተዋህዶ ከማለት ይልቅ ያልቅ ያለመከፋፈል ፤ ያለመነጣጠል ፤ ያለመጠፋፋት ያለመለወጥ /በተሃቅቦ/ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ በተዋህዶ /አሐዱ ባህርይ ዘእግዚአብሔር ቃል ሥግው/ በሚለው እምነት ከአንድነት ደረጃ ላይ ቢደርስ ቤተ ክርስቲያናችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት  የመቀራረን አሳብ የማትቃወም መሆኗን ታረጋግጣለች፡፡
2. መስከረም 22 ቀን 1990 ዓ.ም በወጣው መብሩክ ጋዜጣ ከብፁዕ አብነ ገብርኤል ለፓትርያርኩ የተጻፈ ማሳሰቢያና    ተማጽኖ /ገፅ 4/
3. በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ ያስነቀፈ ከሁለት አመት በፊት በሁለት ቋንቋ የታተመው የሃይማኖትና የቀኖና መፅሀፍ በእግሊዘኛው ክፍል ገጽ 15 ‹‹ እግዚአብሔር በመለኮትና በባህርይ ሶስት ነው›› ተብሎ ተፅፎ በመውጣቱ ብዙ ውግዘትን ያስከተለ በመሆኑ በአስቸኳይ ይታረም:: ታርሞ ከሆነ ደግሞ በቂ ማብራሪያ በሬዲዮ ፤ በቴቪዥንና  በጋዜጣ ነገር ቀደም ብሎ የታተመው መጽሀፍ ተሰብስቦ እንዲቃጠል ይደረግ››
Ø   አቡነ ገብርኤል ከመፅሀ አዘጋጆች አንዱ ሲሆኑ ስለ መፅሀ የሰጡት አስተያየት ይህን ይመስላል፡፡


No comments:

Post a Comment