ከክፍል አስር የቀጠለ
የተወደዳችሁ አንባብያን!
አሁንም እንደተለመደው "ወልድ ዋሕድ"/www.weldwahed.blogspot.com/
ከተሰኘው ብሎግ ላይ ያገኘነውን ጽሁፍ እነሆ ብለናል፡፡
ሙሉ ዘገባው የ"ወልድ ዋሕድ" ክፍል ሃያ ስድስት ነው፡፡
ለዛሬው “ጌታሁን ደምፀ”
የተባሉት የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ መምህር ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትንና፤July 29 2016 በፌስ ቡክ
ገጻቸው ላይ ያስነበኑንን ትምህርት በጣም ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው ለእናንተ ለተዋህዶ ልጆች ማካፈል ስለፈለግን፤ ጽሁፉ ለንባብ እንዲመች
ከማስተካከል በስተቀር በሃሳቡ ላይ ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኋል፡፡ይህ ጽሁፍ አጭር ግን ትልቅ ትምህርት ሰጪ በመሆኑና
በተለይም በነሐሴ አንድ ቀን የእመቤታችንን የእርገቷን መታሰቢያ ጾም ለመጀመር በተዘጋጀንበት ወቅት የተላለፈ መልእክት በመሆኑ ከወዲሁ
እራሳችንን እንድናዘጋጅ የሚያበረታታ ነው፡፡ጾሙን በተገቢው መንገድ ጾመን ከእመቤታችን በረከት እንድናገኝ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን፡፡
አሜን፡፡