Thursday, September 27, 2012

"ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፮

ካለፈው  የቀጠለ...   
“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጡት እንጂ” ኤፌ. ፭፥፲፩       
     የተከበራችሁ  አንባብያን“ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” እና "ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" በሚሉት ርዕሶች  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መሪዎች የቤ/ክ እምነትና ሥርዓቷን ምን እያዛቡ እንደሆነና እንዲሁም እኛ ምዕመናን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የጥፋታቸው ተባባሪ በመሆን ቤ/ክንን ከጸጋ እግዚአብሔር እንድትራቆት ማድረጋችንን በተመለከተ ሰፊ የሆነ ዘገባ ማቅረቤ የሚታወስ  ነው::  ያለንበት ችግር ይህንን ከመሰለ  ከእኛ ምን ይጠበቃል? በሚለው የመፍትሄ ሃሳብ ዙሪያ እንደምንቀጥል ተስፋ በማድረግ በይደር አቆይተነው ነበር:: ይህንንም ችግር እየተመለከተ የሰላም እንቅልፍ የሚተኛ  የተዋህዶ ልጅ ሊኖር ስለማይገባ ምናልባት ያንቀላፋንም ካለን  ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ  “አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስም ያበራልሃል” ኤፌ. 5፥14 ያለውን ቃል ማስታወስ አለብን:: በመሆኑም  መመሪያችን ቃለ  እግዚአብሔር እንደመሆኑ መጠን ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል ወደሚለው የማጠቃለያ ሃሳብ ከመሄዳችን በፊት ጸሎትን በተመለከተ ጥቂት ማሳሰብ እፈልጋለሁ::

"ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፭

ካለፈው  የቀጠለ...
     
     የተከበራችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ቀደም ሲል“ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” ቀጥሎም “ ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ”  በሚሉት ርዕሶች ያስነበብናችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓቷ ምን ያህል እየተበረዘና እየተከለሰ እንደሆነ ሕዝቡም አሕዛቡም በገሃድ የሚያየውንና የሚሰማውን ችግር ሳይጨምር ቤተክርስቲያንን በሚመሩት በፓትርያርኩ በአባ ጳውሎስ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፤ በታላላቅ ሊቃውንትና በቤተ ክህነት ልዩ ልዩ የሃላፊነት ሥራ ላይ በሚገኙ አካላት የተዘጋጁትን ዜና ቤ/ክ ጋዜጣን ፤ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፣ ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት የሚለውን መጽሐፍ  እንዲሁም የአጣሪ ኮሚሽኑን ሪፖርትና ሌሎችንም ተጨባጭ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ  የተዘጋጁ ናቸው::