Sunday, July 15, 2012

“ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፫


“ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ማቴ. ፳፬ .  ካለፈው  የቀጠለ::
      የተከበራችሁ አንባብያን  ባለፈው ጽሁፋችን  በፓትርያርኩ አባ ጳውሎስና የሳቸውን አላማ በሚያስፈጽሙ ጳጳሳትና ሊቃውንት የተዘጋጀውየኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት የተባለው መጽሐፍ ላይ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትን የተሳሳተ ትምህርት የመጽሐፉን ገጽ በመጥቀስ ማስነበባችን ይታወሳል:: ከዚህ  በመቀጠል ደግሞ የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት የሚያፋልሰውን  ጽሁፋቸውን እንመለከታለን::

Monday, July 2, 2012

“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፪


ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ካለፈው  የቀጠለ:
         “የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ትምህርት ትውፊትና ታሪክ ጠብቆ የተዘጋጀ ” የተባለለት መጽሐፍ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ / እምነት፤ሥርዓተ እምልኮትና የውጭ ግንኙነት) ይ ከሰፈሩት ስህተቶች በጥቂቱ ከዚህ በታች እንመለከታለን::

 1/ በገጽ 37 በምዕራፍ 7 ክብረ ቅድስት ድንግል ማርያም በሚለው ርዕስ ሥር እንዲህ ይላል “ እመቤታችን በዘመኗ ከነበሩት ደናግል ተለይታ እግዚአብሄር ከፈጠራት ጀምሮ  በአሳብ ፤ በመናገር ፤ በመስራት ፤ ንጽሐ ጠባይዕ ያላድፈባት ድንግል ናት::“  በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ትልቁን ኑፋቄ የያዘው “ በዘመኗ ከነበሩት ደናግል ተለይታ” የሚለው ሐረግ ነው:: ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለስም አጠራሯ ክብር ምስጋና ይግባትና ምንም እንኳን የሰዎች ትችት ሆነ ስድብ የእመቤታችንን ክብር የሚቀንስ ባይሆንም የነ አባ ጳውሎስ አባባል እመቤታችን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና ታስባ የነበረች ፤ ዓለም ከተፈጠረ በኋላ ደግሞ ለአምላክ እናትነት የተመረጠች ንጽህት ቅድስት የዘላለም ድንግል መሆኗን በሚያመለክቱ  ምሳሌዎችና ትንቢቶች በብዙ ነቢያት ሲነገርላት  ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ መልእኩ ቅዱስ ገብርኤል አምላካችን እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ለማዳን ከእርሷ እንደሚወለድ ባበሰራት ጊዜ  ”እንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ “ ብሎ የሰጠውን ምስክርነት የሚያስተባብል ነው ::