የተከበራችሁ አንባብያን
ባለፈው ጽሁፋችን በፓትርያርኩ አባ ጳውሎስና የሳቸውን አላማ በሚያስፈጽሙ ጳጳሳትና ሊቃውንት የተዘጋጀው“ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ፡ ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት” የተባለው መጽሐፍ ላይ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትን የተሳሳተ ትምህርት የመጽሐፉን ገጽ በመጥቀስ ማስነበባችን ይታወሳል:: ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት የሚያፋልሰውን ጽሁፋቸውን እንመለከታለን::
ለስሙ ክብር ምስጋና ይግባውና ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛው አምላካችን እግዚአብሔርን በባህርይው የሚያውቀው የለም:: ሆኖም አምላክነቱን አውቀን እንድናመልከው አእምሯችን ሊመረመረውና ሊሸከመው በሚችለው መጠን እራሱን ገልጦልናል:: ይህንንም የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ስንመለከት እግዚአብሔር በስም፤ በአካልና በግብር ሦስት ሲሆን በመለኮት ፤ በአገዛዝ ፤ በሥልጣን ፤ በባህርይ ፤ በህልውናና ይህን በመሳሰለው ሁሉ አንድ እንደሆነ ያስተምረናል:: የተነሳንበት ዓላማ የእግዚአብሔር የፀጋው ግምጃ ቤት የሆነችውን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤ/ክንን የሚመሩት ‹‹አባቶች›› ሃይማኖታችንን ምን ያህል እያጠፉት እንደሆነ ለማሳየት ስለሆነ በዚህ ጽሁፍ ጥልቅና ረቂቅ ወደሆነው የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት አንገባም:: ከላይ በተጠቀሰው
መጽሐፍ የእንግሊዝኛው ክፍል በገጽ 15 A. Mystery of the Trinity በሚለው ርዕስ ሥር እንዲህ
ይነበባል:: When
we say they are three in essence, in divinity, in existence and in will, we do
not mean to say three Gods but one God. እንግዲህ
ለስሙ ክብር ምስጋና ይግባውና እንደነሱ አባባል እግዚአብሔር in essence (በሥልጣን) in divinity (በመለኮት
) in
existence (በህልውና) in will ( በፈቃድ)
ሦስት ነው እያሉ መልሰው ደግሞ እንዲህ ስላልን ሦስት አማልክት ማለታችን አይደለም በማለት ለማደናገር ሞክረዋል:: የሚያሳዝን ነው::
እንዲህ ያለ የተሳሳተ ትምህርት የሚያስተምሩትን ሰዎች ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ በም, ፩ ቁ, ፰-፱
እንዲህ ብሎ አውግዟቸዋል::“ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ
የተረገመ ይሁን:: አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ ፤ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ
ይሁን”:: ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩም አባታቸውን ቅ/ጳውሎስን ተከትለው ይህንን መጽሐፍና አዘጋጆቹን አውግዘዋል:: ( “ጆሮ
ያለው መስማትን ይስማ ”) የሚለውን ጽሁፍ ይመልከቱ::
አባ ጳውሎስ “ የምናመልከው ሦስት መለኮትን (ሦስት አማልክትን) ነው ” ብለው አላበቁም:: ( አባባላቸው ሲተረጎም የጣኦትን አምልኮ ይሰበካል):: ከዚህ ጋር አያይዘው
በአዲስ አበባ የተለያዩ አድባራት( ለምሳሌ ካቴድራል ቅድስት ሥላሴ፤ማህደረ
ስብሐት ልደታ ለማርያም ፤ገነተ ጽጌ ቅ/ኡራኤል ---) የራሳቸውን ፎቶ ከቅድስት ሥላሴ፤ ከመድኃኔዓለምና ከእመቤታችን ከቅድስት
ድንግል ማርያም ሥዕላት ጋር በአንድ ሠሌዳ ላይ አስለውና በቤ/ክ አውደ ምህረት አሰቅለው በቦሌ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ደግሞ ልክ እንደ ናቡከደነፆር በራሳቸው ምስል
ሐውልት (ጣዖት ) አሰርተው ምዕመናን ለእሳቸው እንዲሰግዱላችው እያደረጉ
ነው::
ከዚህም ሌላ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ አደጋ ላይ ለሚገኘው የዋልድባ ገዳም
አንዱ የችግሩ መንስኤ የሆኑት በዚያው ገዳም የሚገኙት የቤተ ጣማ ማህበር አባላትም እምነታችው እንደ አባ ጳውሎስ ሦስት መለኮት
ነው ተብለው ይታማሉ:: የሐሜቱንም እውነትነት የሚያረጋጥልን አባ ጳውሎስም ሆኑ የቤተ ጣማ ማህበር የዋልድባ ገዳም በስኳሩ ፋብሪካ
መገንባት ለሚደርስበት ችግር አባሪ ተባባሪ ሆነው መገኘታቸው ነው:: ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስም በሮሜ መልእክቱ ም ፩ ቁ ፳፰ “እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይገባ
አእምሮ አሳልፎ ሰጣችው“ በማለት የተናገረ ው ቃል ተፈጽሞባቸዋል::በቤ/ክ ግን ዛሬም “ብጹዕ ወቅዱስ” እየተባሉ በጸሎትና በቅዳሴ
እየተወደሱ ይገኛሉ ይህም አርዮስን ቅዱስ ከማለት የተለየ አይደለም:: ቤ/ክ በዚህ ሁኔታ የምትቀጥለው እስከ መቼ ነው ብለን መጠየቅና
ለመፍትሄ መነሳት የኛ የተዋህዶ ልጆቸ መንፈሳዊ ግዴታ በመሆኑ ልናስብበት
ይገባል::
እንግዲህ የአባ ጳውሎስ የጥፋት ተልእኮ ተዘርዝሮ ስለማያልቅ አንባቢ እንዳይሰለች ለዛሬው እዚህ ላይ እናቆየውና ቀጣዩን በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን::
No comments:
Post a Comment