Sunday, September 16, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሰላሳ አንድ


ከክፍል ሰላሳ የቀጠለ
የዶግማና የቀኖና ጥሰት በኢ/ኦ/ ተ/ ቤተ ክርስቲያን፤ ክፍል ሰባት
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
      በጥር ወር 1988 ዓ.ም ለሽያጭ የቀረበውና "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፤ሥርዓተ ምልኮትና የውጭ ግንኙነት " በሚል ስያሜ የተዘጋጀው የኑፋቄ መጽሐፍ ያዘጋጁትና የእርማት ሥራውን የሰሩት እነማን እንደሆኑ እንድረዱ በማሰብ ከመጽሐፉ ውስጥ ባገኘነው መሠረት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፡፡