Sunday, September 16, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሰላሳ አንድ


ከክፍል ሰላሳ የቀጠለ
የዶግማና የቀኖና ጥሰት በኢ/ኦ/ ተ/ ቤተ ክርስቲያን፤ ክፍል ሰባት
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
      በጥር ወር 1988 ዓ.ም ለሽያጭ የቀረበውና "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፤ሥርዓተ ምልኮትና የውጭ ግንኙነት " በሚል ስያሜ የተዘጋጀው የኑፋቄ መጽሐፍ ያዘጋጁትና የእርማት ሥራውን የሰሩት እነማን እንደሆኑ እንድረዱ በማሰብ ከመጽሐፉ ውስጥ ባገኘነው መሠረት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፡፡

ሀ/ ይህ መጽሐፍ በፓትርያርኩ በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ ለመዘጋጀቱ፦
     በመጽሐፍ መግቢያ የመጨረሻው አንቀጽ ላይ እንዲህ ይነበባል “…….የቤተክርስቲያኒቱን እምነትና ትምህርት ትውፊትና ታሪክ አጠር ባለ ዝግጅት ጥርት ባለ አጻጻፍ አዘጋጅቶ ማቅረብና ማሳወቅ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ቅዱስነታቸው (አባ ጳውሎስ) በሰጡት መመሪያ መሰረት ይህ የእምነትና ስርዓተ አምልኮት መጽፍ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና በቤተክርስቲያኒቱ ምሁራን ቅንጅት ተዘጋጅቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርምሮ እንዲታተም ተደርጓል::”
ለ/ የመጽፉ አዘጋጆች

1/  ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ                       
2/ ብፁዕ አቡነ አብርሃም       
3/ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል                        
4/ ብፁዕ አቡነ በርተሎዎስ
5/ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል                       
6/ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
7/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ                           
8/ መልእከ  ታቦር ተሾመ
9/ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ                 
10/ መልአከ ሰላም ዳኛቸው ካሳሁን
11/ መጋቢ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ        
12/ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ ገብረ አማኑኤል
13/ መጋቢ ብርሃናት ጎሃጽባህ ጥሩነህ          
14/ መሪጌታ ደጉ ዓለም
15/ መጋቢ ምስጥር ወልደ ሩፋኤል ፈታሂ     
16/ መሪጌታ ጽጌ ዘሪሁን
17/ ሊቀ ስዩማን ራደ  አስረስ 
18/ መምህር ሀ/ማርያም ተናቸው።
ሐ/  መጽሐፉ ረቂቅ ከላይ በተጠቀሱት አባላት ከተዘጋጀ በኋላ ታይቶ (ታርሞ) እንደታተመ ይገልጻል::
አራሚዎቹም የሚከተሉት ናቸው፤
1/መምህር ገብረ ሕይወት                       
2/ መልአከ ገነት ገብረ ሥላሴ አወቀ
3/መምህር ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር        
4/መጋቤ ብሉይ መዘምር ታየ

ቀጣዩን ክፍል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በሌላ ጊዜ እንመለስታለን::
ለዛሬው ይቆየን::




No comments:

Post a Comment