የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣
“ስለጽዮን ዝም አልልም ” በሚለው ርዕስ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች በቅድስት ቤ/ክ ውስጥና
በዙሪያዋ የሚከናወነው ንግድ የተወገዘ እንደሆነ የጌታችንን ወንጌል ጠቅሰን ባቀረብነው ጽሁፍ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኛችሁ ተስፋ በማድረግ
በሶስተኛው ክፍል ደግሞ የዘመናችን የቤ/ክ መሪዎችም ቅድስት ቤ/ክ ከተልእኮዋ ውጪ በዚሁ የንግድ ስራ እንድትሰማራ ያደረጉበትን ሁኔታ እንመለከታለን::
ሐ/ በቅድስት ቤ/ክ የተቋቋሙ የንግድ ማዕከላት
ሁላችንም
እንደምናውቀውና እንደምናየው በአሁኑ ጊዜ እንኳን ረጅም እድሜና ሰፋፊ ቦታ ያላቸው ይቅሩና በቅርብ ጊዜያት የተተከሉት አብያተ ክርስቲያናት
ሳይቀሩ ገና በመቃረቢያ/ መቃኞ/ እያሉ ማለትም ዋናው ቤ/ክ ሳይጀመር በቅድሚያ የሚሰራው የንግድ ቤት ነው::አንጋፋዎቹና ሰፋ ያለ
ቦታና የገንዘብ አቅሙ ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ትላልቅ ፎቆችን እየገነቡ የንግድ ስራውን በሰፊው ሲያከናውኑት ይታያል::
ሁኔታውን በማስተዋል ከተመለከትነው አባቶቻችን ባወረሱን መሰረት ከዋናው
ህንፃ ቤ/ክ በተጨማሪ የሚሰሩት ለቤ/ክ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቢሮዎች ማለትም የሰበካ ጉባኤ ፣ የስብከተ ወንጌል፣የካህናት አስተዳደር፣
የሰ/ት/ቤት አዳራሽና እንዲሁም የጽዋ ማህበራትና የሰንበቴ ቤትን
የመሳሰሉትን እንጂ የንግድ ቤቶችን ሰርተው አላስረከቡንም።