Friday, June 1, 2012

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8 ክፍል 3


4. ፓትርያርኩ የሲኖዶስን ሥልጣን የሚሽርና እራሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ እንዲሰየሙ የሚያደርግ አዲስ ሕግ      አወጡ ለተባለው፤
1. ሚያዚያ 30 ቀን 1988 ዓ.ም ከተዘጋጀው ህገ ቤተ ክርስቲያን
1.1 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 5 የቅዱስ ሲኖዶሱ ሥልጣን ተግባር ተራ ቁ.1 የቅዱስ ሲኖዶሱ በፓትርያርኩ አመራር ሰጪነትና ሰብሳቢነት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡
1.2 ምዕራፍ 5 ቀን አንቀፅ 14 የፓትርያርኩ ከማዕረግ መውረድ ተራ ቁ.2 ‹‹ ፓትርያኩ የተዋህዶ ሃይማኖትን የሚያፋልስ ሕግጋት ቤተ ክርስቲያንን የማይብቅ ማዕረጉን የሚያጎድፍ ሆነ መገኘቱ በተጨባጭ ማስተጃ ሲረጋገጥ በምልአተ ጉበዔ ያለ አንዳች የሃሳብ ልዩነት በቅዱስ ሲኖዶስ ከተጠና በኋላ በቅድስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት ከማዕረጉ ይወርዳል፡፡
1.3 ምዕራፍ 8 አንቀጽ 23 የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ፀሀፊ በሚለው ርዕስ ሥር ተራ ቁ. 3/ለ/ ‹‹የሲኖዶሱ ዋና ፀሀፊ የቅዱስ አባልና ፀሀፊ ሆኖ ተጠቲነቱ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ይሆናል፡፡››
1.4 ምዕራፍ 9 አንቀፅ 25…‹‹ከቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት መካከል በቅ/ፓትርያርኩ አቅራቢነት ሶስት ዕጩዎች ተወዳድረው     በቅ/ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ የተመረጠው የመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በቅዱስ ፓትርያርኩ ይሾማል፡፡
1.5 ምዕራፍ 16 አንቀፅ 33 ‹‹ካሁን በፊት በቅ/ሲኖዶስ ወጥተው የነበሩ ህጎች በዚህ ሕግ ተሻሽለዋል፡፡
·         የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር አደባባይ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ያለው ችግር እንዲያጣራ ህዳር 5 ቀን 1990 ዓ.ም በፓትርያርኩ ሥልጣን የተሰጠው አጣሪ ኮሚሽን አቅሙ የፈቀደውን ያህል ከላይ የተጠቀሰውን ሕግና ሌሎችንም ችግሮች በማጥናት ሁለት ክፍል ያለው ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ከዚህ ውስጥ አዲሱን ህገ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ቀድሞ ከነበሩት ህጎች ጋር እንዲህ ያነፃጽረዋል፡፡
የአጣሪ ኮምሽን ሪፖርት ክፍል አንድ (ሐምሌ 10/1990 ዓ.ም)
4.1.1.1.(2) /ሐ/ ከዚህ አንፃር ያለአንዳች የሃሳብ ልዩነት የሚለው ኃይለ ቃል በአሁኑ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የተጨመረና ፍትሃዊና ዲሰሞክራሲያዊ አሰራርን የሚጋፋ ፤ ለውሳኔ አሰጣጥና ውጤት መገኘት እንቅፋት የሆነ ይዘት ማካተቱን የሚያመለክት ስለሆነ ቅሬታው በአግባቡ መሆኑ ታምኖበታል፡፡
4.1.1.1.2 /መ/ ከዚሁ አንፃር በፓትርያርኩ አመራር ሰጭነት የሚለው ኃይለ ቃል በአሁኑ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የተጨመረና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የመጨረሻው አካል ቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑ ቀርቶ በቅ/ፓትርያርኩ አመራር ሥ የሚገለፅ የበታች አካል እንደሆነ ፤ በአንፃሩም ፓትርያርኩ ከሰብሳቢነት ያለፈ የሲኖዶሱ የበላይነትን የሚያጎናፅፍ ሆኖ ስለሚያመለክት ቅሬታው አግባብነት ያለው መሆኑ ታምኖበታል፡፡
4.1.1.1.3 ከዚህ አንጻር ‹‹ተጠሪነቱ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ይሆናል›› የሚለው ኃይለቃል በአሁኑ ሕገ ቤተ ክርስቲያን የተጨመረ መሆኑና የቅ/ሲኖዶስ ተግባራት በተሟላ መልኩ የሚያስተናግድበትና የሚገልፅበት ጠንካራ ፅ/ቤት ያልተደራጀበት በመሆኑ እንደቅሬታው አቀራረብ መፈፀሙን የሚያመለክት ስለሆነ ቅሬታው በአግባቡ የቀረበ መሆኑ ታምኖበታል፡፡
4.1.2(4) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ የጠቅላ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እጩዎች አቀራረብን አስመልክቶ ‹‹በቅዱስ ፓትርያርኩ ሁለትና ሶስት እጩዎች አቅራቢነት›› ያለውን በተመለከተ በአዲስ ሕገ ቤተ ክርስቲያን የተጨመሩ ኃይለ ቃሎች መሆናቸውንና ጉባኤው እየተቃወመ የተካተቱና አለአግባብ የፀደቁ ተብለው የሚጠቀሱ ዋና ዋና የቅሬታና የውዝግብ ነጥቦች በመሆናቸው እንደገና የሚረቀቀውና የሚፀድቀው ሕገ ቤተ ክርስቲያን በግልፅና ዲሞክራሲያዊ ውይይት ተመርምረው ተገቢውን ውሳኔ ቢያገኙ፡፡
የአጣሪ ኮሚስን ሪፓርት ክፍል ሁለት (ጥቅምት 23 1991 ዓ.ም)
1.2.2 ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አደራጃጀትና አመራር የመወሰንን ስልጣን በተመለከተ፤
v  ገፅ 19 ‹‹… በዚሁ መሠረት ኃላፊዎች ያሳዩት የአመራር ብቃትና ውጤት በአንድ በኩል ከተጣላባቸው ኃላፊነት አኳያ በሌላ በኩል ደግሞ የመንበረ ፓትርያርክ መዋቅራ የስራ ዘርፎች ከሚገኙበት ድክመትና ውድቀት አንጻር በመሆኑ ከፍተኛ የአመራር ድክመት የተመዘገበበት ወቅት ነው ቢባል ተጋነነ አይሆንም፡፡››
v   ገፅ 21… በመሆኑም ያለ እቅድና ፕላን መመራት ብርሀን በሌለበት ጨለማ እንደመጓዝ የሚቆጠር ሲሆን በተፈለገበት ጊዜና በተፈለገው ቦታ የማይደረስበት ለጉዳትና ለችግር የምትጋለጥበት ፤ ተልዕኮዋን በአግባቡ የማትፈፅምበት… በአጠ ቃላይ ከብርሀንና ከጨለማ ጉዞ በማመሳሰል ሊገለፅ የሚችል ነው ለማለት ይቻላል፡፡
v  ገጽ 22፡- ‹‹በዚህ መሠረት አጠቃላይ ችግሩ ሲመዘን 90% የቤተክርስቲያን አስተዳደር ማህበረተሰብ በደል ደረሰብኝ የሚል ቅሬታ ያለው ወገን መሆኑን በዚህ ዙሪያ የችግሩ ተዋናዮችና የበደሉ አራማጆች 10% የማይበልጡ መሆናቸው በኮሚሽኑ ግምገማ የታመነበት ውጤት ነው፡፡
v  ገጽ 23 4.2.3.2፡- በተመሳሳይ ሁኔታ በድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በቤተ-ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ወ.ዘ.ተ የሚፈጸመው ዝውውርና ምደባ አፈጻጸሙ ይህ ነው የሚባል መመዘኛና ስርዓት የሌለው በጉቦ፤ በዝምድና፡ በአድልዎ፤በወገናዊነት፤በጥቅማጥቅም የተመሰረተ መሆኑን ኮሚሽኑ ከቀረበለት አቤቱታ መረጃና ከደረሰበት ጥናራዊ ድምዳሜ አኳያ ለመረዳት ተችሏል፡፡
v  ብፁእ አብነ ገብርኤል አዲሱ ህግ ሲፀድግ አብረው ነበሩ ሲሆን ይህንኑ ህግ በመቃወም ለፓትርይርኩ የጻፉት ማሳሰቢያና ተማፅኖ መስከረም 22 ቀን 1990 ዓ.ም በወጣው መብሩክ ጋዜጣ ገጽ 4 ላይ ከሰፈረው ሃሳብ በከፊል፡-

No comments:

Post a Comment