Thursday, May 31, 2012

“ጆሮ ያለው መሰማትን ይስማ” ሉቃስ 8፡8 ክፍል 4


5. ጳጳሳትና ኤጴስ ቆጶሳት፣ የቤተክርስቲያን አለቆች፣ ካህናትና ዲያቆናት የወጣውን ህግ መቃወም ሲገባቸው የጥፋቱ ተባባሪ ሆነዋል፣ ፓትርያርኩ እንደ አምላክ ያመልካቸዋል ለተባለው፡-
ሀ) ዜና ቤተክርስትያን ጋዜጣ 50ኛ አመት ቁርር 150 ገጽ 10 ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አለቆች ካህናትና ሰራተኖች ለዘመን መለወጫ የደስታ መገለጫዎች ውስጥ የተወሰደ፡-‹‹እንዚሁም የታሪከዊቷ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ርዕሰ መንበር ሲሆኑ ዘይፈቅድ እምኔክሙ ይኩንክሙ ሊቀ ይኩንክሙ ላዕከ ባለው መሰረት መንፈሳዎ ስራዎችዎ በካኅናትና ምዕመናን ዘንድ ሰርፀው ለምልመውና አብበው ፍሬ እንዲያስገኙ እንደ ትጉህ ገበሬ ያለ እረፍት በየቅዱሳን መካናት እየተዘዋወሩ ቃለ ምዕዳንና ትህትናን የተላበሰ መመሪያ በመስጠት የሚያደርጉት ሃዋርያዊ ጥረትና መንፈሳ የስራ ሂደት አዲስ በመሆኑን ስራው አዲስ ከሆነ ደግሞ የስራው ባለቤት የሆኑት ቅዱስ አባታችን አዲስ ሐዋርያ ነዎትና ‹‹ልብስዎ ለሐዲስ ብእሲ›› ያለውን ቃለ ሐዋርያ መነሻ በማድረግ ውስጣዊ ህሊናችንን ከንዋመ ሀኬት ለስራ የሚቀሰቅሰውን ቅዱስ አባት በስራ፤ በምግባር፣ በሃይማኖት እንከተለው ለማለት ጥቅሱን ለመነሻነት ተጠቅመንበታል፡፡››
ለ) ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ 50ኛ ዓመት ቁጥር 163 መስከረም 1 ቀን 1990 ዓ.ም ‹‹የአ/አ፤ አድባራት ገዳማት እራሱን ‹‹መርሀ ተወህዶ›› ብሎ የሚጠራውን ፀረ ቤተ ክርስቲያን ቡድን አውገዙ›› በሚለው ርዕስ ስር የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት የሰንበት ት/ቤት አባላት ፤ የየአጥቢያ ቤ/ክ ሰራተኞች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የቀረበ ፅሁፍ ነው፡- ገፅ 10 እና 13

‹‹ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ሆይ››
          ከላይ በርዕሱ እንደተጠቀሰው ‹‹የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና ለታሰሩትም መፈታትን፤ ለእውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ›› በማለት ነብየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ አስቀምጦታል፡፡ ይህ አባባል የቅዱስነትዎን ያለማመንታት የሚመለከት ነው፡፡ ምክንያቱም የጌታ መንፈስ በቅድስናዎ ላይ አድሮ እንዳባትዎ ዮሐንስ አፈወርቅ ማር በሚጣፍጥ አንደበትዎ ህሊና በሚመስጥ ስብከትዎ ድሀ ሃብታም ሳይለይ የሰው ሃጢአት ከጀርባ ላይ ሲወርድ እየመለከቱ ክብር በተሞላበት እልልታ እየታጀበ ሲያደንቀው አይተናል፡፡
ከዚሁ በመቀጠል ‹‹እግዚአብሔር ስራህን ተቀብሎታል ሂድ እንጀራህን በደስታ ብላ የወይን ጠጅህንም ጠጣ ሁልግዜ ልብስህ ነጭ ይሁን ቅባትም ከራስህ ላይ አይታጣ መክብብ 9፡7›› . . . .  ‹‹. . . ይህም የዘወትር መንፈሳዊ ስራዎ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ልብስህ ነጭ ይሁን በማለት ጥልቅ በሆነ እውቀትዎ እና በመለኮተ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ የሚመሰል ልብሶዎ በደብረ ታቦር የታየው ጉልህ ሚስጢር ነው ስለዚህ እኛ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ልጆችዎ በዛሩው እለት የተጀመረው አመት የሰላም የፍቅርና የጤና እንዲሆንልዎት እየተመኘን ምን ጊዜም ቢሆን በሰራዎ ሆነ በማንኛውም አጋጣሚ ከጎንዎ መሆናችንን እያረጋገጥን ስነ ጹሁፋችንን በዚህ እናበቃለን፡፡
      እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ ከተጠቀሱት የቤ/ክ ጋዜጦች የተወሰዱት ጹሁፎች ስንመለከት የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና ምዕመናን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የተነገሩትን ሀይለ ቃሎች ለፓትሪያርኩ የተነገሩ ናቸው በማት የአምላክነት ክብር ከመስጠታቸውም በላይ በሐይማኖትም ሆነ በስራ ተባባሪነታቸው አረጋግጠዋል፡፡
6. ፓትሪያልኩ በተሾሙ በአመታቸው ማለትም በ1985 ዓ.ም ሮም ሄደው ከፓፓው ጋር የጸሎት የቅዳሴ የመብልና የመሳሰሉት ተሳትፎ አድርገዋል ለተባለው፡- ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ 50ኛ አመት ቁጥር 165 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የውጭ ግንኙነት በሚለው ርእስ ስር ገጽ 3 ተራ ቁጥር 29 “ግንቦት 20 ቀን 1985 ዓ.ም ለ18 ቀናት 5ኛው ፓትርያሪክ ብጹዕ አቡነ ጳውሎ በጄኔቭ በቬየና በቫቲካን ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ ከሐይማኖት መሪዎች ጋር በሰፊው ተወያይተዋል፡፡ በተለይ ቫቲካን በጉብኙበት ወቅት በቫቲካን ቤተ መጽሐፍት የሚገኙ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጥንታዊያን የብራና መጻህፍት ስለሚመለከት ጉዳይ ከፓፓ ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጋር ተወያይተዋል፡፡”
7. ፓትሪያኩ በ1986 ዓ.ም ግሪክ ሄደው ልክ በሮም እንዳደረጉት ተመሳሳይ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ የስርዓቱ ተካፋይ ሆነዋል ለተባለው ከላይ በተጠቀሱት ጋዜጣ ቁጥር  ከ30-50ኛው አመት ቁጥር 165 “ከህዳር 20 እስከ ታህሳስ 5 1986 በቁስጥኝጥያ አቴንስ ሁለቱ ታላላቅ መሪዎች በምስራቅ ኦርቶዶክስና በኦሪየንታል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በኮሚቴው ደረጃ ስለተጀመረው የመቀራረብ ውይይት ጉዳይና ስለ አለም ሰላም በሰፊው ተወያይተዋል፡፡
8. ለፓትሪያሪኩ በ1987 ዓ.ም አሲሲ ሮም ሄደው ከሮማው ፓፓ ጋር ስብሰባ አድርገዋል ለተባለው ከላይ በተጠቀሰው ጋዜጣ 50ኛ አመት ቁ 165 ተራ ቁጥር 31 “ከጳጉሜ 5/1986 እስከ መስከረም 4/1987 ዓ.ም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ በአሲሲ ኢጣሊያ “የእግዚአብሔር ወዳጆች የሰላም ምስክሮች” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ታላላቅ የሐይማኖትና የመንግስት መሪዎች በተገኑበት አለም አቀፍ የሰላም ጉባዔ ላይ ተገኝተው ሰፊ ንግግር አድርገዋል፡፡
9. ፓትሪያሪኩ አቡነ ጳውሎ የፕሮቴስታንት ምሩቅ ስለሆኑ የነሱን አላማ እያስፈጸሙ ነው ለተባለው ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ         50ኛ አመት ቁጥር 164 ብጹዕ አቡነ ጳውሎስ የግሪክን ፓትርያሪክ አነጋገሩ በሚለው ርዕ ስር
ሀ. ገጽ 12 በተለይም ብጹዕ ውቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሰጡት መግለጫ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጋር ያላት ግንኙነትና ወዳጅነት ጥንታዊ መሆኑን አውስተው በአሁኑ ጊዜ ያለውም የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነትና ወዳጅነት ካለረፈው በበለጠ የተጠናከረ መሆኑ ገልጸዋል፡፡”
ለ. በዚሁ ጋዜጣ የአፍቃሪ አብያተ ክርስቲያኖች ጉባዔና ውጤቱ በሚለው ርእስ ስር
1.      ከመስከረም 24-30 1990 ዓ.ም በአፍሪቃ አዳራሽ አፍሪቃ አብያተ ክርስቲያናት ጉባዔ መካሄዱን፣
2.     በአቡነ ጳውሎስ መሪነት መስከረም 24/1990 እኩለ ቀን ላይ ከ147 የአፍሪካ አገሮች የመጡ የመናፍቃን ድርጅቶች ተወካዮች፣ ኢትዮጵያ የቤ/ክ አስተዳዳሪዎች ምዕመናን ካህናት ዲያቆናት የሰ/ት/ቤት ወጣቶች እንዲሁም የተለያዩ የመናፍቃን ድርጅቶች መሪዎችና አባላቶች ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በተገኙበት የጉባዔው መክፍቻ ጸሎት መደረጉን
3.     መስከረም 25 ቀን 1990 ዓ.ም በቅድስተ ሥላሴ ቤ/ክ ሁሉም የጉባዔው ተሳታፊዎች ማለት የ147 አገሮች የሐይማኖት መሪዎች በተገኙበት  የቅዳሴ ጸሎት መደረጉን በጋዜጣው ገጽ 1፣7፣8፣9፣ በዝርዝር ቀርቧል፡፡
ሐ. ዜና ቤ/ክ ጋዜጣ 50ኛ አመት ቁ.165 የውጭ ግንኙነት አስፈላጊነት በሚል ርእስ ሥር ገጽ 5… የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በዓለም ላይ ያለች ቤተክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ከራስዋ ወጪ ስለሌላው ማወቅም ማየትም መስማትም የለብኝም በሚል የብቸኝነትና የምናኔ ጠባይ ደጅዋን ዘግታ የተቀመጠች ቤ/ክአይደለችም----፡፡ በዚሁ ርዕስ ፊደል “ሐ” ስር “ከጊዜ በኋላ የተፈጠረውን የቤ/ክ መከፋፈል በማስወገድ ወደ ቀደመው አንድነት ለመለስ የሚቻልበት ሁኔታ መሞከር----“፡፡
መ. ዜና ቤ/ክ ጋዜጣ 50ኛ ዓመት ቁ.167 ገጽ 1 እና ገጽ 10 “የከርበንተሪው ሊቀ ጳጳሳት የኢትዮጵያን ቤ/ክ በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡
ሠ. ዜና ቤ/ክ ጋዜጣ 50ኛ አመት ቁ 170 ገጽ 1 እና 11 “የቅ/ፓትርያሪኩ የሩሲያን ተጠባባቂ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተቀብለው አነጋገሩ” በሚለው ርእስ ሥር፣ “ቅዱስነታቸው አክለው በሩሲያ ኦርቶዶክስና በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መካከል ያለው ግንኙነት በአሁኑ ወቅት ይበልጥ እየጠጠናከረ መምጣቱንና ይህ በሁለቱ ሕዝች መካከል ያለው ግንኙነት በአሁኑ ወቅት ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱንና ይህ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ለሚደረገው ሁለገብ ትብብር የበኩሉን እስተዋጽኦ እንደሚያበረክት--- የመል መቋቋም መርሃ ግብር ያለው ተመሳሳይነት በመንፈሳዊውም ሆነ በማህበራዊ አብረው ለመስራትና ለመረዳዳት ምቹ እንደሚሆን አስገልዝበዋል፡፡
10. ከእስላም ከካቶክና ከፕሮቴስታንት ጋር በመተባበር ፡ ሁሉንም አባቶች ናቸው በማለት በአገሪቱ ላይ አራት አይነት ሃይማኖት አውጀውባታል ለተባለው፡-ዜና ቤ/ክ ጋዜጣ 50ኛ አመት ቁ.172 ገጽ 11ጦርነቱ እንዲቆም የሃይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ አቀረቡ” በሚለው ርዕስ ስ፡- “በኢትዮጵያ የሚገኙ (1) የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ (2) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት(3) የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤ/ክ (4) የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ  የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር መሪዎች፣የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ምሁራን----”  ገጽ 7 ላይ “በዚሁ ሲምፖዚየም ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የመክፈቻ ቃለ ቡራኬ፣ አራቱ የሃይማኖት ድርጅቶች ተወካዮች ጥናታዊ ጹሁፍ አቅርበዋል፡፡
11. ጥር 1 ቀን 1989 ዓ.ም በቅ/እስጢፋኖስ ቤ/ክ አውደ ምህረት የተገደሉት ባህታዊ፤ እንዲሁም ጥር 4 ቀን 1989 ዓ.ም በቅ/ዩሐንስ ቤ/ክ የተፈጸመው ወንጀል በአደባባይ የተደረገ ስለሆነ ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ አይደለም፡፡
12. ሐምሌ 5 ቀን 1991 ዓ.ም በሰኞ ዕለት በቀይ ልብስ መሾማቸው የካቶሊክ ሥርዓት ነው ለተባለው ዜና ቤክ ጋዜጣ 50ኛ አመት 184 ላይ ከጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠው መግለጫ ከኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በዕለት ሰኞ ለመደረጉ የተለያዩ ምክንያቶች ቀርበዋል፡፡ ለመጥቀስ ያህል ከገጽ 11‹‹የ5ኛው ፓትርያሪክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ርአሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዓለ ሲመት የሚከበረው በየዓመቱ ሐምሌ 5 ቀን ነው፡፡ መተ ኤጲስ ቆጳሳቱም በዚሁ እለት ሊከናወን የቻለው ይህን ተደራራበ የቤተክርስቲያን በዓል በማስመርኮዝ የቀረበው ትችትና ነቀፋ ለቤተ ክርስቲያን እቆረቆራለሁ ከሚል ሰው ሊቀርብ የሚገባ አይደለም::”ከዚህም ሌላ የቀረበው ምክንያት በፍትሐ ነገስት ሹመቱ አሁድ ይሁን የተባለው ብዙ ሰው የሚሰበስብበት ስለሆነ እንጂ ሌላ ምክንያት የለውም፡፡ በሰው ብዛት በኩል በዚህ እለትም ከእለተ እሁድ ያላነሰ ሰው ስለተገኘ ሰኞ መደረጉ ስህተት አይደለም ብሏል ቤተክህነት ፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ በፍትሀ ነገስት ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ስለ ኤጲስ ቆጶስ ሹመት የተፃፈበት ክፍል በገጽ 70 ያለውን በከፊል እንመልከት፡፡
      “ሐዋሪያት በዲዲስቅሊያስ በ37ኛ አንቀጽ ኤጲስ ቆጶስ እሁድ ቀን ይሾ አሉ ሀተታ አምስቱን ቀን በስራ ይሰነብታሉ ቅዳሜ የተጣላ ያስታርቃሉ እሁድ እሁድ ይሰበሰባሉና ሁሉ እንዲያውቁት ዕሁድ ቀን ይሾም አሉ፡፡ አንድም ቀኒቱ ደግ እንደሆነች ሹመቲቱም ደግ ናትና አንድም ጌታ በእለተ እሁድ የተሸመውን ሹመት የሚሾም ነውና ወእምአመ ሐደረ ቃል ውስተ ስጋ አሚን አስተርአያ እንዲሉ አንድም አኮኑ ኃምስ  መካልየ ዘወሀብከኒ ወረባህኩ ዲቤሆን ሀምስ መካልየ ብሎ የሚያስረክብበት ቀን ናትና ይህንንም ስሀቅ መነኮሰ ስንኳን መንፈሳዊ ሹመት ስጋዊ ሹመት ቅሉ በእለተ እሁድ ይሁን ብሏል፡፡”       
      እንግዲህ ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወቅታዊ ችግር በዋናነት የተቃወሙትና የገዙቱት አለቃ ኤሌው ይሁኑ እንጂ ከላይ እንደተመለከትነው የአለቃ አባባል ትክክል መሆኑን ሌላው ቀርቶ የራሱ የቤተክህነት ልሳን የሆነው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ እንኳን ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ በሌላ አቅጣጫ ቤተ ክህነት አለቃ አያሌውን እንዲህ ይላቸዋል፡፡
      ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ 50ኛ ዓመት ቁ.184 “ክህነት ሳይኖር ውግዘት” በሚል ርዕስ ስር ገጽ 11 “አለቃ አያሌው ምንጊዜም እውነትን ተናግሮ አያውቅም  የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ከሮማው ፓፓ ጋር አብረው ቀደሱ ፣ የሮም ቤተ ክርስቲያን አባልነት አጸደቁ፤ወዘተ የሚለው ሁሉ በአልጋው ላይ ተንቶ የሚቃዥው ቅዥት ነው፡፡ሌላውንም እንደ ራሱ በመቁጠር ለማታለል የሚያወራውና የሚያስወራው ከመሆኑ በቀር ቅንጣት ያህል እውነት የለውም፡፡” ይላል
  ከላይ በመግቢያው እንደተገለጸው የሚሰማ ጆሮ ያለው በትክክል የሚያይ ዓይንና የሚያስተውል ልቡና ያለው ማንም ሰው እውነቱ የትኛው እንደሆነ መለየት  አያዳግተውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከተጠቀሱት ጋዜጦቸውና መጽሄቶች እንዲሁም መፃህፍት ሌላ በተለያዩ አበይት በዓላት አከባበር ላይ የሚታዩ ብዙ ስህተቶችም ይስተዋላሉ፡፡ ለምሳሌ ለቃና ዘገሊላ በኣል ታቦቱ ከጥምቀተ ባህር ተመልሶ ሳይገባ የቅዳሴ ስርዓት ተፈጽሟል፡፡ ይህን የመሳሰሉ ብዙ አሉ፡፡
     እንግዲህ የዘመናችን የቤተ ክርስቲያን ችግር ምን እንደሚመስል ለማመልከት ያህል በየመገናኛ ብዙኋን የሚታየውንና የሚሰማውን ችግር ሳይጨምር በጹሁፍ ከሰፈረውም በጣም ጥቂቱን ብቻ ተመልከተናል፡፤ ነገሩን ለማጠቃለል አለቃ አያሌው ግዝትን በየደረጃው ያስተላለፉበትን ዋና ዋና ምክንያት ከዚህ ቀጥሎ እንመልከት፡፡
1.      ፓትርያሪኩ አቡነ ጳውሎስን የገዘቱበት ምክንያት
ሀ.ሚስጥረ ስላሴ፤ ሚስጥረ ስጋዌን፤ ነገረ ማርያምን እና ቀኖና ቤተ ከውርስቲያን የሚያፋልስ መጽሀፍ በመጻፋቸው
ለ. እስከዛሬ ቤተ ክርስቲያን ስትመራበት የነበረውን ሕግ ሽረው እራሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ የሚያስቀምጥ አዲስ ሕግ በማውጣታቸው
ሐ. አባቶቻችን ካወገዟቸው የካቶሊክና የፕሮቴስታንት የእምነት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ቤተክርስቲ የነሱ ጥገኛ በማድረጋቸውና ሌሎችም
2.   ሌሎችን ጳጳሳት የገዘቱበት ምክንያት፡-
ሀ. የተወሰኑት ከፓትርሪኩ ጋር በመሆን በዋናነት ከላይ የተጠቁትን ጥፋቶች በመፈጸማቸውና በማስፈጸማቸው
ለ. ሌሎች ደግሞ ችግሩ የገባቸው የተወሰነ ተቃውሞ ቢያስሙም እስከ መጨረሻ ታግለው ምዕመናን  በማስተባበር ወደ መፍትሔ መድረስ ባለመቻላቸው
3.   የቤተ ክርስያን አስተዳዳሪዎችን፤ ካህናትና ዲያቆናትን የገዘቱበት ምክንያት
ሀ) ከላይ እንዳየነው እንደ ሲኖዶስ አባላት ከፓትርያሪኩ ጎን በመቆም ችግሩ መፍትሔ እንዳያገኝ እና ምዕመናንንም ስለ ቤተክርስቲያን ችግር እንዳይናገሩ በማፈናቸው
ለ) አንዳንድ ችግሩ የገባቸው ቢሆኑም ምን እንበላለን በሚል የምንቸገረኝነት መንፈስ በዝምታ በመመልከታቸው
ሐ) ከላይ የተጠቀሱትን ጥፋቶች በመፈጸማቸው የተወገዙትን፤ ፓትርያሪክ ቅዱስ ብሎ በጸሎትና በቅዳሴ ስማቸውን በመጥራታቸው
4.   ምዕመናንን የገዘቱበት ምክንያት
ሀ) አንዳን ምዕመናን በተለይ የሰበካ ጉባዔ ተመራጮችና የሰንበት ት/ቤት ተመራጮች ከላይ እንደተጠቀሱት ጳጳሳትና ካህናት የጥፋት ተባባሪ በመሆናቸው፤
ለ) በገንዘቡም ሆነ በማንኛውም ጉዳይ ቤተክርስቲያን የሚያስተዳድሩት ምዕመናን መሆናቸውና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው አግልግሎትም ተጠቃሚ የሆኑት ያው ምዕመናን መሆናቸው እየታወቀ ሃይማኖትና ስርዓት ሲበላሽ እያዩ ዝም በማለታቸው
ሐ) ከላይ የተገለጡ ጥፋቶች የሚሰሩት በምዕመናን ገንዘቡና ጉልበት በመሆኑ ቢያንስ ለጥፋተኞች ገንዘብና ድጋፍ ባለመስጠት ችግሩን መቀነስ ሲቻል ባለመደረጉና ሌሎችም ናቸው፡፡
       ይህንን ስንመለከት ከደቂቅ እስከ ልሒቅ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሚሰራው ጥፋት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን በስም ካልሆነ በስተቀር በተግባር ወይም በእውነት አለች ለማለት አያስደፍርም:: ቤተ ክረስቲያንን በከበረ ደሙ ፈሳሽነት የመሰረታት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ምንም ብትፈተን እንደማጠፋ ቃል ኪዳን ስለገባላት በቸርነቱ ታደጋታ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ሆኖም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ቤተክርስቲን ለመታደግ ሌቦችንና ወንበዴዎችን ለማባረር በሚያነሳው ጅራፍ ከመገረፍ የሚድን ካለ እሱ ብጹዕ ነው፡፡
                                   የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ቤተ ክርሰቲያንን
                                   በሃይማኖት እንድትከፈት ያድርግልን::
    ማስታወሻ
ይህ የማገናዘቢያ ጹሁፍ የተዘጋጀው እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ ያለውን ብቻ የሚመለከት ነው፡፡

No comments:

Post a Comment