Friday, June 15, 2012

“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፩


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ አሜን
“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ክፍል ፩
                                 ማቴ, ፳፬ ቁ, ፬

         በዚህ ጽሑፍ በጥር ወር 1988 ዓ.ም  ”የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፤ሥርዓተ እምልኮትና የውጭ ግንኙነት ”በሚል ስያሜ የተዘጋጀው መጽሐፍ  ”ሦስት መለኮት“ ከሚለው  ጀምሮ በውስጡ የያዘውን ጎላ ጎላ ያለ ስህተትና ይህንኑ መሰረት በማድረግ የተፈጠሩትን ችግሮች የምንመለከት ሲሆን በቅድሚያ ግን ይህንን የክህደት መጽሐፍ ታዘጋጁት እነማን እንደሆኑ እናያለን::
ሀ/ ይህ መጽሐፍ በፓትርያርኩ በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ ለመዘጋጀቱ፦
በመጽሐፍ መግቢያ የመጨረሻው አንቀጽ ላይ እንዲህ ይነበባል “ ,,,,የቤተክርስቲያኒቱን እምነትና ትምህርት ትውፊትና ታሪክ አጠር ባለ ዝግጅት ጥርት ባለ አጻጻፍ አዘጋጅቶ ማቅረብና ማሳወቅ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ቅዱስነታቸው (አባ ጳውሎስ) በሰጡት መመሪያ መሰረት ይህ የእምነትና ስርዓተ አምልኮት መጽሀፍ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና በቤተክርስቲያኒቱ ምሁራን ቅንጅት ተዘጋጅቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርምሮ እንዲታተም ተደርጓል::”
ለ/ የመጽሀፉ አዘጋጆች
1/  ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ                       2/ ብፁዕ አቡነ አብርሃም       
3/ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል                        4/ ብፁዕ አቡነ በርተሎዎስ
5/ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል                        6/ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
7/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ                           8/  መልእከ  ታቦር ተሾመ
9/ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ                   10/ መልአከ ሰላም ዳኛቸው ካሳሁን
11/ መጋቢ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ                 12/ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ ገብረ አማኑኤል
13/ መጋቢ ብርሃናት ጎሃጽባህ ጥሩነህ            14/ መሪጌታ ደጉ ዓለም
15/ መጋቢ ምስጥር ወልደ ሩፋኤል ፈታሂ        16/ መሪጌታ ጽጌ ዘሪሁን
 17/   ሊቀ ስዩማን ራደ  አስረስ                 18/ መምህር ሀ/ማርያም ተደላ ናቸው።

ሐ/  ከላይ በተጠቀሱት አባላት ከተዘጋጀ በኋላ
1/ መምህር ገብረ ሕይወት                        2/ መልአከ ገነት ገብረ ሥላሴ አወቀ
3/ መምህር ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር          4/ መጋቤ ብሉይ መዘምር ታየ  ባሉበት መጽሐፉ ታይቶ (ታርሞ) እንደታተመ ይገልጻል::
ቀጣዩን በሌላ ጊዜ እንመለስባታለን:: ይቆየን::

No comments:

Post a Comment