የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣
በቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ውስጥና ዙሪያ የሚተከሉ የልማት ተቋማትና የንግድ ማእከላት÷ ሐዋርያዊ አገልግሎትዋን በዘላቂነት የሚደግፍ ቋሚ የገቢ ምንጭ የመፍጠር፣ የካህናቷን የኑሮ ኹኔታ የማሻሻል፣ የምግባረ ሠናይ ተግባራትን በስፋት የማከናወንና ከልመና የምንወጣበትን ስልት የመቀየስ፤ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያናችንን የፋይናንስ አቅም በማሳደግ በራሷ ምእመናን ልማት ላይ የተመሠረተ ሉዓላዊ ክብሯን ለመጠበቅ ተግቶ የመሥራት ዓላማ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
የፕሮጀክቶቹ መርሖዎችም፡- ሥርዐትና ትውፊት የጠበቁ ንዋያተ ቅድሳትን፣ የኅትመትና የጥበበ እድ ውጤቶችን፣ የስጦታና የግንባታ ዕቃዎችን ለማምረትና ለማከፋፈል፣ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን በዕውቀት የበለጸገና በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት ቅድሚያ መስጠት፤ የማኅበረሰቡን ጥቅምና ሀገራዊ ማንነት ታሳቢ ማድረግ፤ ለብዝሐ ሕይወት አዎንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከት፤ የምርትና የአገልግሎት ዋጋ ፍትሐዊነትና ምክንያታዊነት ሊኾን ያስፈልጋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ደጅ፣ ቅጥርና ገረገራ÷ የሰላም ደጅ፣ የሰላም በር – ደጀ ሰላም ነውና፡፡
(ሰንደቅ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፬፻፺፪፤ የካቲት ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት ለግለሰቦች የሚያከራዩዋቸው በርካታ የንግድ ማዕከላት/ሱቆች/ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅምና በሚያስተች አኳኋን ለሦስተኛ ወገን በከፍተኛ ጥቅም እየተላለፉ (ቁልፋቸው እየተሸጠ) እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
በሀገረ ስብከቱ ገዳማትና አድባራት ይዞታ ውስጥ የሚገኙ መሬቶችንና ሕንፃዎችን ኪራይና አጠቃቀም በመፈተሽ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ ጥቅም የሚሰጡባቸውን መንገዶች የሚያመቻች ጥናት ለማቅረብ የተቋቋመው ኮሚቴ እያካሔደ ባለው የማጣራት ሥራ፣ ግለሰቦች ከአድባራቱ የሚከራዩዋቸው አብዛኛዎቹ የንግድ ማእከላት/ሱቆች/ ‹‹እጅግ በጣም አሳዛኝ በኾነ መንገድ የተከራዩና ለሦስተኛ ወገን የተሸጡ››ሲኾን የመካነ መቃብር ይዞታም እየተቆረሰ ከዓላማው ውጭ መዋሉ እንደተረጋገጠ ተመልክቷል፡፡
በተመረጡ 69 አድባራትና ገዳማት ላይ የጀመረውን ጥናት በድርጊት መርሐ ግብሩ መሠረት እያከናወነና ግብዓት ሊኾኑ የሚችሉ መረጃዎችንም እያሰባሰበና እያደራጀ እንደሚገኝ የገለጸው ኮሚቴው፣ ጥር ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአቀረበው ማሳሰቢያ÷ አፋጣኝ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ያላቸው አሳሳቢ ችግሮች በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኩል መመሪያና ማስተካከያ እንዲሰጥባቸው ጠይቋል፡፡
የጥናቱን ውጤት ተከትሎ የሚመጣውን የአሠራር ለውጥና ማስተካከያ ሳይጠብቁ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር አፋጣኝ መመሪያ ሊሰጣቸው ይገባል ከተባሉት አድባራት መካከል የቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በሚሳለምበት የደብሩ ዋና መግቢያ በር ግራና ቀኝ፣ የመጠጥ ግሮሰሪዎችና የሴቶች የውበት ሳሎን ተከፍተው የተከራዩ ሲኾኑ ተከራዩ ደግሞ ለሦስተኛ ወገን በከፍተኛ ጥቅም አከራይቷቸዋል፡፡ ይህም ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮና ሥርዐት አንጻር የማይደገፍና እምነቱን የሚያስተች ከመኾኑም በላይ ምእመኑን ለቁጣ እንዳነሣሣው ተገልጧል፡፡
የሱቆቹ ውሎች ተቋርጦ ቦታው ነጻ ይደረግ ዘንድ መመሪያ እንዲሰጥ የጠየቀው ኮሚቴው፣ ደብሩ ባለው ሰፊ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ባዶ ቦታዎች ሕጋዊ ባልኾነ አግባብ ሊከራዩ የሚችልበት ዕድል እንደሚኖር በማሳሰብ ጥናቱ እስኪጠናቀቅና ተለዋጭ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ የደብሩ አስተዳደር ምንም ዓይነት የኪራይ ውል እንዳይዋዋል ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍለት አመልክቷል፡፡
ደብሩ ለመካነ መቃብር አገልግሎት የተሰጠው ቦታ ተቆራርሶ ለሌሎች አገልግሎቶች የተከራየ ሲኾን ይህም ‹‹ያለጨረታ፣ በጣም አሳዛኝ በኾነ ዋጋ›› መፈጸሙን ኮሚቴው በጥናቱ አጣርቷል፡፡ ቦታው ከአገልግሎቱ ውጭ በሕገ ወጥ መንገድ ለመኪና ማቆሚያና ለጋራዥ መዋሉ ይዞታውን እንደሚያጣብበና በመንግሥት ሊያስነጥቅ እንደሚችል የጠቆመው ኮሚቴው፣ ተከራዮች እንዲለቁና ቦታው በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ይውል ዘንድ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ አሳስቧል፡፡
በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል፣ በጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል እና በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ አብያተ ክርስቲያንየተሠሩ የንግድ ሱቆች ለተከራይ አከራይ ወይም ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው የተከራዩ (ቁልፋቸው የተሸጠ) መኾኑን የየአድባራቱ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤያቱ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ ዋና ጸሐፊዎች፣ ቁጥጥሮችና ሒሳብ ሹሞች በተገኙበት መረጋገጡ ታውቋል፡፡
ለዛሬው ይቆየን ::
“ስለጽዮን ዝም አልልም ” በሚለው ርዕስ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ክፍሎች በቅድስት ቤ/ክ ውስጥና በዙሪያዋ የሚከናወነው ንግድ የተወገዘ እንደሆነ የጌታችንን ወንጌል ጠቅሰን ባቀረብነው ጽሁፍ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
በተለይም በሶስተኛው ክፍል፡-
ተመልክተን በይቀጥላል አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም በተለያዩ የግል ማህበራዊ ጉዳዮች ምክንያት ለተወሰኑ ጊዜያት ብንዘገይም ለዚህ ጊዜ ያደረሰንን ልዑል እግዚአብሔርን እያመሰገንን ከዚህ ቀጥሎ ‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ከተሰኘው ድረ ገጽ ላይ ያገኘነውን ጽሁፍ እንድታነቡ እንጋብዛለን፡፡ ‹‹ከድጡ ወደ ማጡ›› እንዲሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተልዕኮዋ ውጪ በንግድ ሥራ ላይ መሰማራቷ አነሶ ሀብትና ንብረቷ በማናለብኝና በአሳፋሪ ሁኔታ እየተዘረፈ ለግለሰቦች መጠቀሚያ፤እንዲሁም ደግሞ ለመናፍቃን መጠቋቆሚያ እየሆነች ነው፡፡
- ለንግድ ሥራ በተሰሩት ህንጻዎችና ሱቆች አብያተ ክርስቲያናቱ መሸፈናቸውን ፤
- ለልማቱ ሲባል በክብር ያረፉ የክርስቲያኖች አጽሞች ከአፈር ጋር እየተፈነቀሉ መጣላቸው፤
- በየንግድ ቤቶቹ ውስጥ አጸያፊና ኢክርስቲያናዊ ነገሮች እየተፈጸሙ መሆናቸውን፤
- የንግድ ቤቶቹን የሚከራዩት ከሃይማኖታችን ውጪ የሆኑ ሰዎችም ጭምር መሆናቸው፤
- የእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን የገቢ መጠን መዛባት የሚያመጣውን አሉታዊ ተጽእኖ ፤ወ.ዘ.ተ
February 15, 2015
‹‹ቤተ
ክርስቲያንን በማይጠቅምና በሚያስተች አኳኋን ለሦስተኛ ወገን የሚተላለፉ የአድባራት የንግድ ማዕከላት ኪራይ አሳሳቢ ኾኗል››
በምስሉ የሚታዩት የቢራ ማስታወቂያዎችን የያዙ የመጠጥ ግሮሰሪዎች፣ የውበት ሳሎን፣ ባርና ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለምንና የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል አብያተ ክርስቲያንን ደጀ ሰላም፣ ቅጥርና ገረገራ ይዘው የሚታዩ የንግድ ማዕከላት ናቸው፡፡
በቃለ ዐዋዲው አንቀጽ ፲፪ ንኡስ አንቀጽ (፯) እና (፰) በቤተ ክርስቲያን ስም ውል ስለመዋዋል በተለይም በቋሚ ንብረቶችና ግምታቸው ከፍተኛ ስለኾኑ የኪራይ ውሎች የተደነገገውን በመተላለፍ የቦታውን ዋጋ በአገናዘበ አኳኋን በሕጋዊ መንገድ ከአለመከራየታቸውም በላይ በተከራይ አከራይ ለሦስተኛ ወገን በከፍተኛ ጥቅም የተላለፉት እኒኽ የንግድ ማዕከላት፣ በቤተ ክርስቲያን መሳለሚያና መዳረሻ በሮች ለአገልግሎት መዋላቸው ምእመኑን እያሳዘነውና እያስቆጣው ይገኛል፡፡በቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ውስጥና ዙሪያ የሚተከሉ የልማት ተቋማትና የንግድ ማእከላት÷ ሐዋርያዊ አገልግሎትዋን በዘላቂነት የሚደግፍ ቋሚ የገቢ ምንጭ የመፍጠር፣ የካህናቷን የኑሮ ኹኔታ የማሻሻል፣ የምግባረ ሠናይ ተግባራትን በስፋት የማከናወንና ከልመና የምንወጣበትን ስልት የመቀየስ፤ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያናችንን የፋይናንስ አቅም በማሳደግ በራሷ ምእመናን ልማት ላይ የተመሠረተ ሉዓላዊ ክብሯን ለመጠበቅ ተግቶ የመሥራት ዓላማ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
የፕሮጀክቶቹ መርሖዎችም፡- ሥርዐትና ትውፊት የጠበቁ ንዋያተ ቅድሳትን፣ የኅትመትና የጥበበ እድ ውጤቶችን፣ የስጦታና የግንባታ ዕቃዎችን ለማምረትና ለማከፋፈል፣ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን በዕውቀት የበለጸገና በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት ቅድሚያ መስጠት፤ የማኅበረሰቡን ጥቅምና ሀገራዊ ማንነት ታሳቢ ማድረግ፤ ለብዝሐ ሕይወት አዎንታዊ አስተዋፅኦ ማበርከት፤ የምርትና የአገልግሎት ዋጋ ፍትሐዊነትና ምክንያታዊነት ሊኾን ያስፈልጋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ደጅ፣ ቅጥርና ገረገራ÷ የሰላም ደጅ፣ የሰላም በር – ደጀ ሰላም ነውና፡፡
(ሰንደቅ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፬፻፺፪፤ የካቲት ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት ለግለሰቦች የሚያከራዩዋቸው በርካታ የንግድ ማዕከላት/ሱቆች/ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅምና በሚያስተች አኳኋን ለሦስተኛ ወገን በከፍተኛ ጥቅም እየተላለፉ (ቁልፋቸው እየተሸጠ) እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
በሀገረ ስብከቱ ገዳማትና አድባራት ይዞታ ውስጥ የሚገኙ መሬቶችንና ሕንፃዎችን ኪራይና አጠቃቀም በመፈተሽ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ ጥቅም የሚሰጡባቸውን መንገዶች የሚያመቻች ጥናት ለማቅረብ የተቋቋመው ኮሚቴ እያካሔደ ባለው የማጣራት ሥራ፣ ግለሰቦች ከአድባራቱ የሚከራዩዋቸው አብዛኛዎቹ የንግድ ማእከላት/ሱቆች/ ‹‹እጅግ በጣም አሳዛኝ በኾነ መንገድ የተከራዩና ለሦስተኛ ወገን የተሸጡ››ሲኾን የመካነ መቃብር ይዞታም እየተቆረሰ ከዓላማው ውጭ መዋሉ እንደተረጋገጠ ተመልክቷል፡፡
በተመረጡ 69 አድባራትና ገዳማት ላይ የጀመረውን ጥናት በድርጊት መርሐ ግብሩ መሠረት እያከናወነና ግብዓት ሊኾኑ የሚችሉ መረጃዎችንም እያሰባሰበና እያደራጀ እንደሚገኝ የገለጸው ኮሚቴው፣ ጥር ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአቀረበው ማሳሰቢያ÷ አፋጣኝ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ያላቸው አሳሳቢ ችግሮች በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኩል መመሪያና ማስተካከያ እንዲሰጥባቸው ጠይቋል፡፡
የጥናቱን ውጤት ተከትሎ የሚመጣውን የአሠራር ለውጥና ማስተካከያ ሳይጠብቁ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር አፋጣኝ መመሪያ ሊሰጣቸው ይገባል ከተባሉት አድባራት መካከል የቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በሚሳለምበት የደብሩ ዋና መግቢያ በር ግራና ቀኝ፣ የመጠጥ ግሮሰሪዎችና የሴቶች የውበት ሳሎን ተከፍተው የተከራዩ ሲኾኑ ተከራዩ ደግሞ ለሦስተኛ ወገን በከፍተኛ ጥቅም አከራይቷቸዋል፡፡ ይህም ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮና ሥርዐት አንጻር የማይደገፍና እምነቱን የሚያስተች ከመኾኑም በላይ ምእመኑን ለቁጣ እንዳነሣሣው ተገልጧል፡፡
የሱቆቹ ውሎች ተቋርጦ ቦታው ነጻ ይደረግ ዘንድ መመሪያ እንዲሰጥ የጠየቀው ኮሚቴው፣ ደብሩ ባለው ሰፊ ይዞታ ውስጥ የሚገኙ ባዶ ቦታዎች ሕጋዊ ባልኾነ አግባብ ሊከራዩ የሚችልበት ዕድል እንደሚኖር በማሳሰብ ጥናቱ እስኪጠናቀቅና ተለዋጭ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ የደብሩ አስተዳደር ምንም ዓይነት የኪራይ ውል እንዳይዋዋል ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍለት አመልክቷል፡፡
ደብሩ ለመካነ መቃብር አገልግሎት የተሰጠው ቦታ ተቆራርሶ ለሌሎች አገልግሎቶች የተከራየ ሲኾን ይህም ‹‹ያለጨረታ፣ በጣም አሳዛኝ በኾነ ዋጋ›› መፈጸሙን ኮሚቴው በጥናቱ አጣርቷል፡፡ ቦታው ከአገልግሎቱ ውጭ በሕገ ወጥ መንገድ ለመኪና ማቆሚያና ለጋራዥ መዋሉ ይዞታውን እንደሚያጣብበና በመንግሥት ሊያስነጥቅ እንደሚችል የጠቆመው ኮሚቴው፣ ተከራዮች እንዲለቁና ቦታው በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ይውል ዘንድ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ አሳስቧል፡፡
በቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን 17 ሱቆች በብር 1500 ለአንዲት
ግለሰብ የተከራዩ ሲኾን ግለሰቧም ለሌሎች በማከራየት በወር ከብር 30‚000 በላይ በማግኘት እንደሚጠቀሙ ተገልጧል፡፡ የደብሩ አስተዳደር
ኹኔታውን በመቃወም ውላቸው እንዲቋረጥ ለማድረግ በክሥ ላይ የሚገኝ ቢኾንም ሀገረ ስብከቱ ውሉ እንዲታደስ የሚያስገድድ ደብዳቤ ለደብሩ
መጻፉ ለውዝግብ መንሥኤ እንደኾነና ለማጣራት ሥራውም ዕንቅፋት መፍጠሩን ኮሚቴው ያስረዳል፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለግለሰብ በማድላት
ደብሩ ውል እንዲዋዋል የሚያስገድደው የሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ እንዲነሣና ደብሩ ይዞታውን እንዲያስከብር መመሪያ እንዲሰጥ ኮሚቴው
ጠይቋል፡፡
በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል፣ በጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል እና በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ አብያተ ክርስቲያንየተሠሩ የንግድ ሱቆች ለተከራይ አከራይ ወይም ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው የተከራዩ (ቁልፋቸው የተሸጠ) መኾኑን የየአድባራቱ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤያቱ ምክትል ሊቃነ መናብርት፣ ዋና ጸሐፊዎች፣ ቁጥጥሮችና ሒሳብ ሹሞች በተገኙበት መረጋገጡ ታውቋል፡፡
በመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ለኪራይ ከዋሉት 55 ሱቆች ውስጥ 50ዎቹ ለሦስተኛ ወገን ተከራይተዋል(ቁልፋቸው ተሽጠዋል)፡፡ የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ኹለት ታላላቅና 13 ታናናሽ ሱቆች ያሉት ሲኾን አብዛኞቹ ከ5 – 10 ለሚኾኑ ዓመታት ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው የተከራዩ ናቸው፡፡ ለመኪና መመርመሪያ በሚል ከደብሩ በካሬ ብር 6.00 ሒሳብ ለዐሥር ዓመት የተከራየው ግለሰብ ብር 18‚000 ወርኃዊ ኪራይ ለደብሩ የሚከፍል ቢኾንም ተከራዩ መጋዘን ሠርቶበት ለሦስተኛ ወገን በማከራየት በወር ከብር 50‚000 በላይ ያገኛል፡፡
ከመሬት ኪራይ፣ ከሱቅ ኪራይና ከመካነ መቃብር ጋራ በተያያዘ በርካታ ችግሮች የታዩበት የደብሩ አስተዳደር፣ የተሰጠውን መመሪያ በመጣስ አዲስ ሱቅ ሠርቶ ለማከራየት እየተንቀሳቀሰ መኾኑን የገለጸው ኮሚቴው፣ ለሕገ ወጥ ሥራው በሀገረ ስብከቱ በኩል ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ሱቆች ባለቤት ቢኾንም ኹሉም ለማለት በሚያስደፍር አኳኋን በሕጋዊ መንገድ ያልተከራዩ፣ በተከራዮች ለሦስተኛ ወገን ተላልፈው (ቁልፋቸው ተሽጦ) በዕጥፍ የተከራዩ መኾናቸው ተገልጧል፡፡
የጥናት ተልእኮውን በሰነዶች ምርመራና በግምገማ ስልቶች እያከናወነ የሚገኘው ኮሚቴው፣ በየሱቆቹ በመዘዋወር የተከራይ አከራዮችን በማነጋገር ግልጽ መረጃዎችን መሰብሰቡን ገልጾ፣ የሦስተኛ ወገን ተከራዮች ለኮሚቴው ግልጽ መረጃዎችን በመስጠታቸው አንዳችም ችግር እንደማይደርስባቸው የየአብያተ ክርስቲያኑ አለቆች እንዳረጋገጡላቸው ጠቅሷል፡፡ ይኹን እንጂ ለኮሚቴው ግልጽ መረጃ የሰጡት የሦስተኛ ወገን ተከራዮች በአከራዮቻቸው ጫና እየደረሰባቸው ከመኾኑም በላይ የየአድባራቱ አለቆች በገቡላቸው ቃል መሠረት ከጫናው ሊታደጓቸው አልቻሉም ብሏል፡፡
ይህ አካሔድ የኮሚቴውን ቀጣይ የጥናት ሥራና የጥናቱን ውጤት ለችግር የሚያጋልጠው በመኾኑ የሦስተኛ ወገን ተከራዮች በአከራዮቻቸውም ይኹን በደብሩ ምንም ዐይነት ጫና እንዳይደርስባቸው፣ ተለዋጭ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስም ባሉበት ኹኔታ እየሠሩ እንዲቆዩ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንዲጻፍላቸው ኮሚቴው በማሳሰቢያው ጠይቋል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ለጥናቱ የሚያደርጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚደነቅና የሚመሰገን ነው ብሏል – ኮሚቴው፡፡ ይኹንና የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር በአንድ በኩል በመሬትና በንግድ ተቋማት ኪራይ ዙሪያ የተጀመረውን ጥናት ተከትሎ ምንም ዐይነት የኪራይ ውል ይኹን ግንባታ እንዳይካሔድ ታግዶ ሳለ፣ የኪራይ ጨረታና ውል እንዲካሔድ የሚያስገድድ ደብዳቤ መጻፉ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያን መመሪያውን እንዲቃወሙና ውዝግብ እንዲነሣ ምክንያት ኾኗል፡፡
በሌላ በኩል የጥናት ኮሚቴው ስለመቋቋሙና ስለተልእኮው የሚገልጸውንና ለተመረጡት 69 አድባራት ማድረስ የሚገባውን ደብዳቤ በማዘግየትና ቆራርጦ በመበተን ዕንቅፋት ፈጥሯል፡፡ በዚኽ ረገድ ለጥናቱ ዐይነተኛ ማሳያ የሚኾኑ ግብዓቶች እንደሚገኙበት ለሚታመንበት ለገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ደብዳቤው ባለመዘጋጀቱና ባለመድረሱ ኮሚቴው ለእንግልት መዳረጉ ተጠቅሷል፤ በሀገረ ስብከቱ በጥቅም ትስስር የተንሰራፋው ግብረ ሙስና ማረጋገጫም ነው ተብሏል፡፡
በመኾኑም የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ዕንቅፋትና ውዝግብ ከሚፈጥሩ መሰል ተግዳሮቶች እንዲታቀብና ጥናቱን ከመደገፍና ከማስተባበር አኳያ ተገቢውን ትእዛዝ ለአድባራቱ በወቅቱ እንዲያስተላለፍ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በኩል ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጠው ኮሚቴው በአጽንዖት ጠይቋል፡፡ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከጥናት ኮሚቴው በዝርዝር የቀረቡት አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች በሙሉ ተግባር ላይ ውለው አፈጻጸማቸው እንዲገለጽለት የካቲት ፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በቁጥር 2599/357/2007 በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡
የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት በአሳዛኝ አደጋ ላይ እንደኾነ በተጠቆመበት ጥናታዊ ሒደቱ÷ የቤተ ክርስቲያን መሬት ከአካባቢ ዋጋ በታችበካሬ ከ0.37 – 0.50 ሳንቲም ከ10 – 15 ዓመታት በማከራየት ከፍተኛ ምዝበራ እየተፈጸመ ስለመኾኑ ተረጋግጦበታል፤ የኪራይ ውላቸው ከተፈተሹ የንግድ ማዕከላት ከዘጠና በመቶ ያላነሱቱ ከተገቢው የኪራይ ዋጋቸው በታች እስከ 10 ዓመታት በተከራዩት ግለሰቦች ለሦስተኛ ወገን በኹለትና ሦስት ዕጥፍ በኪራይ በመተላለፋቸው ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለተከራይ ግለሰቦች የሚያደሉና የቤተ ክርስቲያን ጥቅም ተላልፎ የተሰጠባቸው መኾናቸው ታውቋል፡፡
የአድባራቱ የሰነዶች አያያዝና አደረጃጀት በአሳፋሪና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተስተውሏል፤ በመረጃ አሰጣጥ ረገድ አጥኚ ልኡካኑን ለመዋሸትና ለመደበቅ የሞከሩ ጥቂቶች አይደሉም፤ የጥናቱን ዓላማ ከአለመረዳት ጀምሮ ልኡካኑን በነዳጅና ውሎ አበል ስም በመደለያ የማባበል ዝንባሌዎችም ታይተዋል፡፡ በአንጻሩ ጠንካራ ሰበካ ጉባኤያት ባሉባቸው አድባራት የቦታና የሱቅ ኪራይ ውሎች የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ ጠብቀው፣ የፋይናንስ ሕጉንና ደንቡን አክብረው የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ጥቅም በሚያስጠብቅ አኳኋን መፈጸማቸው ተገልጧል፡፡ ለዚኽምእንደ አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት ያሉ አድባራት በአርኣያነት ተጠቅሰዋል፡፡
ባለፈው ታኅሣሥ መባቻ ሥራውን የጀመረው ኮሚቴው ለጥናት ከመረጣቸው 69 አድባራት ውስጥ እስከ አኹን ከ18 ያላነሱትን ዳስሷል፡፡ ሒደቱ በተወሰኑ ቀናት ልዩነት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ባሉበት እየተገመገመ አቅጣጫ እንደሚሰጥበት ተነግሯል፡፡ በተቻለ መጠን እንዲቀላጠፍ ትእዛዝ የተሰጠበት ይኸው ጥናት በመሬትና በንግድ ተቋማት ኪራይ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች አሳይቶ የመፍትሔ ሐሳቦችን እንደሚጠቁም የሚጠበቅ ሲኾን ይህም ቤተ ክርስቲያን የመሬት አጠቃቀምና የኪራይ ተመን ፖሊሲ ለማውጣት እንደሚያስችላት ተስፋ ተደርጓል፡፡
ለዛሬው ይቆየን ::
No comments:
Post a Comment