Sunday, March 8, 2015

ስለ ጽዮን ዝም አልልም!!! ኢሳ.62፥1 ክፍል አራት

ካለፈው የቀጠለ
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣
 “ስለጽዮን ዝም አልልም ” በሚለው ርዕስ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ክፍሎች በቅድስት ቤ/ክ ውስጥና በዙሪያዋ የሚከናወነው ንግድ የተወገዘ እንደሆነ የጌታችንን ወንጌል ጠቅሰን ባቀረብነው ጽሁፍ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

በተለይም በሶስተኛው ክፍል፡-
  1. ለንግድ ሥራ በተሰሩት ህንጻዎችና ሱቆች አብያተ ርስቲያናቱ መሸፈናቸውን ፤
  2. ለልማቱ ሲባል በክብር ያረፉ የክርስቲያኖች አጽሞች ከአፈር ጋር እየተፈነቀሉ መጣላቸው
  3. በየንግድ ቤቶቹ ውስጥ አጸያፊና ኢክርስቲያናዊ ነገሮች እየተፈጸሙ መሆናቸውን፤
  4. የንግድ ቤቶቹን የሚከራዩት ከሃይማኖታችን ውጪ የሆኑ ሰዎችም ጭምር መሆናቸው
  5. የእያንዳንዱ ቤርስቲያን የገቢ መጠን መዛባት የሚያመጣውን አሉታዊ ተጽእኖ ፤ወ.ዘ.ተ
ተመልክተን በይቀጥላል አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም በተለያዩ የግል ማህበራዊ ጉዳዮች ምክንያት ለተወሰኑ ጊዜያት ብንዘገይም ለዚህ ጊዜ ያደረሰንን ልዑል እግዚአብሔርን እያመሰገንን ከዚህ ቀጥሎ ‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ከተሰኘው ድረ ገጽ ላይ ያገኘነውን ጽሁፍ እንድታነቡ እንጋብዛለን፡፡ ‹‹ከድጡ ወደ ማጡ›› እንዲሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተልዕኮዋ ውጪ በንግድ ሥራ ላይ መሰማራቷ አነሶ ሀብትና ንብረቷ በማናለብኝና በአሳፋሪ ሁኔታ እየተዘረፈ ለግለሰቦች መጠቀሚያ፤እንዲሁም ደግሞ ለመናፍቃን መጠቋቆሚያ እየሆነች ነው፡፡

Thursday, July 25, 2013

ስለ ጽዮን ዝም አልልም!!! ኢሳ.62፥1 ክፍል ሶስት

ካለፈው የቀጠለ
       የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣

ን ዝም አልልም ” በሚለው ርዕስ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች በቅድስት ቤ/ክ ውስጥና በዙሪያዋ የሚከናወነው ንግድ የተወገዘ እንደሆነ የጌታችንን ወንጌል ጠቅሰን ባቀረብነው ጽሁፍ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኛችሁ ተስፋ በማድረግ በሶስተኛው ክፍል ደግሞ የዘመናችን የቤ/ክ መሪዎችም ቅድስት ቤ/ክ ከተልእኮዋ ውጪ  በዚሁ የንግድ ስራ እንድትሰማራ ያደረጉበትን ሁኔታ እንመለከታለን::

ሐ/ በቅድስት ቤ/ክ የተቋቋሙ የንግድ ማዕከላት

        ሁላችንም እንደምናውቀውና እንደምናየው በአሁኑ ጊዜ እንኳን ረጅም እድሜና ሰፋፊ ቦታ ያላቸው ይቅሩና በቅርብ ጊዜያት የተተከሉት አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀሩ ገና በመቃረቢያ/ መቃኞ/ እያሉ ማለትም ዋናው ቤ/ክ ሳይጀመር በቅድሚያ የሚሰራው የንግድ ቤት ነው::አንጋፋዎቹና ሰፋ ያለ ቦታና የገንዘብ አቅሙ ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ትላልቅ ፎቆችን እየገነቡ የንግድ ስራውን በሰፊው ሲያከናውኑት ይታያል:: ሁኔታውን በማስተዋል ከተመለከትነው አባቶቻችን ባወረሱን  መሰረት ከዋናው ህንፃ ቤ/ክ በተጨማሪ የሚሰሩት ለቤ/ክ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቢሮዎች ማለትም የሰበካ ጉባኤ ፣ የስብከተ ወንጌል፣የካህናት አስተዳደር፣ የሰ/ት/ቤት አዳራሽና  እንዲሁም የጽዋ ማህበራትና የሰንበቴ ቤትን የመሳሰሉትን  እንጂ የንግድ ቤቶችን ሰርተው አላስረከቡንም።

Monday, April 15, 2013

ስለ ጽዮን ዝም አልልም!!! ኢሳ.62፥1 ክፍል ሁለት

ካለፈው የቀጠለ
     የተከበራችሁ የቅድስት  ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች
     ባለፈው ስለ ጽዮን ዝም አልልም በሚለው ርዕስ ሥር የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርት " በሚለው ንዑስ  ርዕስ በቤ/ልንፈጽማቸው ከማይገቡ ተግባራት አንዱ የሆነውን የንግድ ሥራ በቅጥረ / እንዳንፈጽም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስያስተማረንንና ወንጌላውያንም የጻፉልንን በጥቂቱ ተመልክተን በይደር አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል::ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ይህንንየጌታችንን ቃል በድፍረት ተራምደው ቅድስት /ክንን የንግድ ማዕከል ያደረጉዋትን ክፍሎች በሦስት ከፍለን የምንመለከታቸው ሲሆንከሁሉ አስቀድመን ልንገነዘበው የሚገባን የንግዱ ተዋናዮች ማለትም ሻጮችም ሆኑ ገዢዎቹ የዚችው የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆችመሆናቸውን ነው፡፡
     የዚህ ርዕስ ዓላማ በቤ/ ምንም ዓይነት የንግድ ሥራ መከናወን እንደሌለበት ማስገንዘብ ስለሆነ ነጋዴዎች ለሕብረተሰቡየሚያቀርቡትን የሸቀጥ ዝርዝር ማቅረብ አስፈላጊ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ቁጥሩ ከመብዛቱ የተነሳ ጸሐፊውንም ሆነ አንባቢውንከማሰልቸት በቀር ሌላ ጥቅም የለውም፡፡ሆኖም ለችግሩ አጽንኦት እንዲሰጠውና ወደ መፍትሔውም ለመሄድ አንዲቻል በጥቂቱ መጥቀሱግድ ነው፡፡ ነጋዴዎች መደበኛ ሥራቸው ንግድ ስለሆነ ምዕመናኑ ለዕለት ከዕለት ኑሮው የሚፈልጋቸውን ሸቀጦች ለይተው ያውቃሉ፡፡እነዚህም ከእርጥብ በሶቢላ ጀምሮ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ አዳዲስና ያገለገሉ ልብሶችና ጫማዎች፣የውበት ዕቃዎች፣ የቤትዕቃዎች፣የተለያዩ ሎተሪዎች እንዲሁም ለባዕድ አምልኮ አገልግሎት የሚውሉ የጢሳ ጢስ ዓይነቶችን ሳይቀሩ በስፋት ተዘርግተው ሲሸጡይታያል፡፡

Sunday, January 13, 2013

ስለ ጽዮን ዝም አልልም!!! ኢሳ.62፥1 ክፍል አንድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
“የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ ፤አንባቢው ያስተውል…”ማቴ.24፥15

    የተከበራችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች፦ እንደምን ሰንብታችኋል? በቸርነቱና በቅዱሳኑ ቃል ኪዳን እየጠበቀ እዚህ ያደረሰን ፈጣያችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ  እስከ ዘለዓለም ድረስ የተመሰገነ ይሁን፡፡ “ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ ” እና “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ” በሚት ርዕሶች በቤ/ክ ስም የተዘጋጁ ነገር ግን የቤ/ክንን እምነትና ሥርዓት እንዲሁም ትውፊቷን ሳይቀር የሚያፋሱትን መጻሕፍት በመጥቀስ የተዘጋጀውን ሰፊ ዘገባ እንደተመለከትን ሁሉ በዚህም ርዕስ ደግሞ በቅድስት ቤ/ክ ሊደረጉ የማይገባቸው ነገር ግን በስፋት እየተፈጸሙ ያሉትን ­­­­­­­­­­­ጥፋቶች እንመለከታለን፡፡የዚህም ጽሑፍ አዘጋጅ ዋና ዓላማ ሁላችን የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ወደ ማስተዋል ተመልሰን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከምንሰራው ስህተት እንድንመለስ ለማሳሰብ ነው፡፡   
   ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ለማሳለፍ የሚመጣበት ጊዜ ሲቃረብ የሚታዩትን ምልክቶች ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝርዝር የነገራቸውን በወንጌል ስናነብ (በማቴ.24፥1-ፍጻሜ፤ ማር.13፥1-ፍጻሜ፤ ሉቃ.21፥5-36 ) እኛ ያለንበት ዘመን ትንቢቶቹ በብዛት እየተፈጸሙ እንደሆነ ያመለክተናል፡፡ከነዚህም የዓለም ፍጻሜ የመቃረቡ ምልክቶች አንዱ “የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ ፤አንባቢው ያስተውል…ማቴ.24፥15 በማለት ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ትንቢት ነው፡፡ጌታችንም ይህንን ትምህርት ያስተማረው አስቀድሞ ነቢዩ ዳንኤል  የተናገረውን  በመጥቀስ ሲሆን ትንቢቱም እንዲህ የሚል ነው፡፡ “ከእርሱም ጋር ሠራዊቶች ይቆማሉ ፤መቅደሱንም ግንቡንም ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ የጥፋትንም ርኩሰት ያቆማሉ፡፡” ዳን.11፥31 ፡፡ ይህ የርኩሰት ሥራ በኢአማንያኑ ብቻ የሚፈጸም ቢሆን ባላሰደነቀም ነበር፡፡የበለጠ የሚያሳዝነው ግን ቤ/ክ እናከብራለን የምንለው ሰዎች የእግዚአብሔርን ማደሪያ ቅድስት ቤ/ክንን በተለያየ ነገር እያረከስናት መሆኑ ነው፡፡ከነዚህም ጥፋቶች ውስጥ በቅድሚያ አንዱን ብቻ እንመለከታለን፡፡

Thursday, September 27, 2012

"ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፮

ካለፈው  የቀጠለ...   
“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጡት እንጂ” ኤፌ. ፭፥፲፩       
     የተከበራችሁ  አንባብያን“ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” እና "ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" በሚሉት ርዕሶች  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መሪዎች የቤ/ክ እምነትና ሥርዓቷን ምን እያዛቡ እንደሆነና እንዲሁም እኛ ምዕመናን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የጥፋታቸው ተባባሪ በመሆን ቤ/ክንን ከጸጋ እግዚአብሔር እንድትራቆት ማድረጋችንን በተመለከተ ሰፊ የሆነ ዘገባ ማቅረቤ የሚታወስ  ነው::  ያለንበት ችግር ይህንን ከመሰለ  ከእኛ ምን ይጠበቃል? በሚለው የመፍትሄ ሃሳብ ዙሪያ እንደምንቀጥል ተስፋ በማድረግ በይደር አቆይተነው ነበር:: ይህንንም ችግር እየተመለከተ የሰላም እንቅልፍ የሚተኛ  የተዋህዶ ልጅ ሊኖር ስለማይገባ ምናልባት ያንቀላፋንም ካለን  ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ  “አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስም ያበራልሃል” ኤፌ. 5፥14 ያለውን ቃል ማስታወስ አለብን:: በመሆኑም  መመሪያችን ቃለ  እግዚአብሔር እንደመሆኑ መጠን ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል ወደሚለው የማጠቃለያ ሃሳብ ከመሄዳችን በፊት ጸሎትን በተመለከተ ጥቂት ማሳሰብ እፈልጋለሁ::

"ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፭

ካለፈው  የቀጠለ...
     
     የተከበራችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ቀደም ሲል“ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” ቀጥሎም “ ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ”  በሚሉት ርዕሶች ያስነበብናችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓቷ ምን ያህል እየተበረዘና እየተከለሰ እንደሆነ ሕዝቡም አሕዛቡም በገሃድ የሚያየውንና የሚሰማውን ችግር ሳይጨምር ቤተክርስቲያንን በሚመሩት በፓትርያርኩ በአባ ጳውሎስ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፤ በታላላቅ ሊቃውንትና በቤተ ክህነት ልዩ ልዩ የሃላፊነት ሥራ ላይ በሚገኙ አካላት የተዘጋጁትን ዜና ቤ/ክ ጋዜጣን ፤ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፣ ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት የሚለውን መጽሐፍ  እንዲሁም የአጣሪ ኮሚሽኑን ሪፖርትና ሌሎችንም ተጨባጭ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ  የተዘጋጁ ናቸው::

Tuesday, August 14, 2012

"ማንም እንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፬

"ማንም እንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ካለፈው  የቀጠለ...
      የተከበራቸሁ አንባብያን ከላይ በተጠቀሰው ርእስ በሶስት ክፍሎች እንዳነበባችሁት በፓትርያርኩ በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ስም የተዘጋጀው  የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት፣ ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት የተባለው የኑፋቄ መጽሀፍ በነገረ ማርያምና በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት ላይ የሚያስተላልፈውን የተሳሳተ መልእክት ከብዙው በጥቂቱ ማቅረባችን ይታወሳል። በዚህ ጽሁፍ  ደግሞ የምሥጢረ ሥጋዌን ትምህርት የሚያፋልሰውን ክፍል እንመለከታለን::