Sunday, January 13, 2013

ስለ ጽዮን ዝም አልልም!!! ኢሳ.62፥1 ክፍል አንድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
“የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ ፤አንባቢው ያስተውል…”ማቴ.24፥15

    የተከበራችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች፦ እንደምን ሰንብታችኋል? በቸርነቱና በቅዱሳኑ ቃል ኪዳን እየጠበቀ እዚህ ያደረሰን ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ  እስከ ዘለዓለም ድረስ የተመሰገነ ይሁን፡፡ “ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ ” እና “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ” በሚሉት ርዕሶች በቤ/ክ ስም የተዘጋጁ ነገር ግን የቤ/ክንን እምነትና ሥርዓት እንዲሁም ትውፊቷን ሳይቀር የሚያፋልሱትን መጻሕፍት በመጥቀስ የተዘጋጀውን ሰፊ ዘገባ እንደተመለከትን ሁሉ በዚህም ርዕስ ደግሞ በቅድስት ቤ/ክ ሊደረጉ የማይገባቸው ነገር ግን በስፋት እየተፈጸሙ ያሉትን ­­­­­­­­­­­ጥፋቶች እንመለከታለን፡፡የዚህም ጽሑፍ አዘጋጅ ዋና ዓላማ ሁላችን የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ወደ ማስተዋል ተመልሰን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከምንሰራው ስህተት እንድንመለስ ለማሳሰብ ነው፡፡   
   ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ለማሳለፍ የሚመጣበት ጊዜ ሲቃረብ የሚታዩትን ምልክቶች ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝርዝር የነገራቸውን በወንጌል ስናነብ (በማቴ.24፥1-ፍጻሜ፤ ማር.13፥1-ፍጻሜ፤ ሉቃ.21፥5-36 ) እኛ ያለንበት ዘመን ትንቢቶቹ በብዛት እየተፈጸሙ እንደሆነ ያመለክተናል፡፡ከነዚህም የዓለም ፍጻሜ የመቃረቡ ምልክቶች አንዱ “የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ ፤አንባቢው ያስተውል…”ማቴ.24፥15 በማለት ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ትንቢት ነው፡፡ጌታችንም ይህንን ትምህርት ያስተማረው አስቀድሞ ነቢዩ ዳንኤል  የተናገረውን  በመጥቀስ ሲሆን ትንቢቱም እንዲህ የሚል ነው፡፡ “ከእርሱም ጋር ሠራዊቶች ይቆማሉ ፤መቅደሱንም ግንቡንም ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ የጥፋትንም ርኩሰት ያቆማሉ፡፡” ዳን.11፥31 ፡፡ ይህ የርኩሰት ሥራ በኢአማንያኑ ብቻ የሚፈጸም ቢሆን ባላሰደነቀም ነበር፡፡የበለጠ የሚያሳዝነው ግን ቤ/ክ እናከብራለን የምንለው ሰዎች የእግዚአብሔርን ማደሪያ ቅድስት ቤ/ክንን በተለያየ ነገር እያረከስናት መሆኑ ነው፡፡ከነዚህም ጥፋቶች ውስጥ በቅድሚያ አንዱን ብቻ እንመለከታለን፡፡

Thursday, September 27, 2012

"ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፮

ካለፈው  የቀጠለ...   
“ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጡት እንጂ” ኤፌ. ፭፥፲፩       
     የተከበራችሁ  አንባብያን“ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” እና "ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" በሚሉት ርዕሶች  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መሪዎች የቤ/ክ እምነትና ሥርዓቷን ምን እያዛቡ እንደሆነና እንዲሁም እኛ ምዕመናን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የጥፋታቸው ተባባሪ በመሆን ቤ/ክንን ከጸጋ እግዚአብሔር እንድትራቆት ማድረጋችንን በተመለከተ ሰፊ የሆነ ዘገባ ማቅረቤ የሚታወስ  ነው::  ያለንበት ችግር ይህንን ከመሰለ  ከእኛ ምን ይጠበቃል? በሚለው የመፍትሄ ሃሳብ ዙሪያ እንደምንቀጥል ተስፋ በማድረግ በይደር አቆይተነው ነበር:: ይህንንም ችግር እየተመለከተ የሰላም እንቅልፍ የሚተኛ  የተዋህዶ ልጅ ሊኖር ስለማይገባ ምናልባት ያንቀላፋንም ካለን  ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ  “አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስም ያበራልሃል” ኤፌ. 5፥14 ያለውን ቃል ማስታወስ አለብን:: በመሆኑም  መመሪያችን ቃለ  እግዚአብሔር እንደመሆኑ መጠን ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል ወደሚለው የማጠቃለያ ሃሳብ ከመሄዳችን በፊት ጸሎትን በተመለከተ ጥቂት ማሳሰብ እፈልጋለሁ::

"ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፭

ካለፈው  የቀጠለ...
     
     የተከበራችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ቀደም ሲል“ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” ቀጥሎም “ ማንም አንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ”  በሚሉት ርዕሶች ያስነበብናችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓቷ ምን ያህል እየተበረዘና እየተከለሰ እንደሆነ ሕዝቡም አሕዛቡም በገሃድ የሚያየውንና የሚሰማውን ችግር ሳይጨምር ቤተክርስቲያንን በሚመሩት በፓትርያርኩ በአባ ጳውሎስ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፤ በታላላቅ ሊቃውንትና በቤተ ክህነት ልዩ ልዩ የሃላፊነት ሥራ ላይ በሚገኙ አካላት የተዘጋጁትን ዜና ቤ/ክ ጋዜጣን ፤ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፣ ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት የሚለውን መጽሐፍ  እንዲሁም የአጣሪ ኮሚሽኑን ሪፖርትና ሌሎችንም ተጨባጭ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ  የተዘጋጁ ናቸው::

Tuesday, August 14, 2012

"ማንም እንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፬

"ማንም እንዳያስታቸሁ ተጠንቀቁ" ማቴ ፳፬ ቁ. ፬ ካለፈው  የቀጠለ...
      የተከበራቸሁ አንባብያን ከላይ በተጠቀሰው ርእስ በሶስት ክፍሎች እንዳነበባችሁት በፓትርያርኩ በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ስም የተዘጋጀው  “የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት፣ ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት” የተባለው የኑፋቄ መጽሀፍ በነገረ ማርያምና በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት ላይ የሚያስተላልፈውን የተሳሳተ መልእክት ከብዙው በጥቂቱ ማቅረባችን ይታወሳል። በዚህ ጽሁፍ  ደግሞ የምሥጢረ ሥጋዌን ትምህርት የሚያፋልሰውን ክፍል እንመለከታለን::

Sunday, July 15, 2012

“ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፫


“ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ካለፈው  የቀጠለ::
      የተከበራችሁ አንባብያን  ባለፈው ጽሁፋችን  በፓትርያርኩ አባ ጳውሎስና የሳቸውን አላማ በሚያስፈጽሙ ጳጳሳትና ሊቃውንት የተዘጋጀው“ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ፡ ስርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት” የተባለው መጽሐፍ ላይ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትን የተሳሳተ ትምህርት የመጽሐፉን ገጽ በመጥቀስ ማስነበባችን ይታወሳል:: ከዚህ  በመቀጠል ደግሞ የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት የሚያፋልሰውን  ጽሁፋቸውን እንመለከታለን::

Monday, July 2, 2012

“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፪


“ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ካለፈው  የቀጠለ:
         “የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ትምህርት ትውፊትና ታሪክ ጠብቆ የተዘጋጀ ” የተባለለት መጽሐፍ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፤ሥርዓተ እምልኮትና የውጭ ግንኙነት) ላይ ከሰፈሩት ስህተቶች በጥቂቱ ከዚህ በታች እንመለከታለን::

 1/ በገጽ 37 በምዕራፍ 7“ ክብረ ቅድስት ድንግል ማርያም ” በሚለው ርዕስ ሥር እንዲህ ይላል “ እመቤታችን በዘመኗ ከነበሩት ደናግል ተለይታ እግዚአብሄር ከፈጠራት ጀምሮ  በአሳብ ፤ በመናገር ፤ በመስራት ፤ ንጽሐ ጠባይዕ ያላድፈባት ድንግል ናት::“  በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ትልቁን ኑፋቄ የያዘው “ በዘመኗ ከነበሩት ደናግል ተለይታ” የሚለው ሐረግ ነው:: ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለስም አጠራሯ ክብር ምስጋና ይግባትና ምንም እንኳን የሰዎች ትችት ሆነ ስድብ የእመቤታችንን ክብር የሚቀንስ ባይሆንም የነ አባ ጳውሎስ አባባል እመቤታችን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና ታስባ የነበረች ፤ ዓለም ከተፈጠረ በኋላ ደግሞ ለአምላክ እናትነት የተመረጠች ንጽህት ቅድስት የዘላለም ድንግል መሆኗን በሚያመለክቱ  ምሳሌዎችና ትንቢቶች በብዙ ነቢያት ሲነገርላት  ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ መልእኩ ቅዱስ ገብርኤል አምላካችን እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ለማዳን ከእርሷ እንደሚወለድ ባበሰራት ጊዜ  ”እንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ “ ብሎ የሰጠውን ምስክርነት የሚያስተባብል ነው ::

Friday, June 15, 2012

“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ማቴ. ፳፬ ቁ. ፬ ክፍል ፩


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ አሜን
“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” ክፍል ፩
                                 ማቴ, ፳፬ ቁ, ፬

         በዚህ ጽሑፍ በጥር ወር 1988 ዓ.ም  ”የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እምነት፤ሥርዓተ እምልኮትና የውጭ ግንኙነት ”በሚል ስያሜ የተዘጋጀው መጽሐፍ  ”ሦስት መለኮት“ ከሚለው  ጀምሮ በውስጡ የያዘውን ጎላ ጎላ ያለ ስህተትና ይህንኑ መሰረት በማድረግ የተፈጠሩትን ችግሮች የምንመለከት ሲሆን በቅድሚያ ግን ይህንን የክህደት መጽሐፍ ታዘጋጁት እነማን እንደሆኑ እናያለን::