Saturday, August 18, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሃያ ስምንት

ከክፍል ሃያ ሰባት የቀጠለ
የዶግማና የቀኖና ጥሰት በኢ/ኦ/ ተ/ ቤተ ክርስቲያን፤ ክፍል አራት
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
ባለፉት ሦስት ተከታታይ ክፍሎች (ከ25-27) በስምምነቱ መግለጫ በተራ ቁ.2 "ስለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት" በሚለው ርዕስ ውስጥ የተወሰኑ ሃሳቦችን ተመልክተናል፡፡በዚህ ክፍል ደግሞ ፤ቃለ ውግዘትን በተመለከተ እንቀጥላለን፡፡
መልካም ንባብ!

Wednesday, August 15, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሃያ ሰባት

ከክፍል ሃያ ስድስት የቀጠለ
የዶግማና የቀኖና ጥሰት በኢ/ኦ/ ተ/ ቤተ ክርስቲያን፤ ክፍል ሦስት
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
ሀ/ "የቀኖና ጥሰት" የቀጠለ
       ባለፉት ሁለት ክፍሎች በስፋት እንደተመለከትነው፤በተደጋጋሚ "የቀኖና ጥሰት" እየተባለ የሚነገረው "ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም" በሚለው ዙሪያ ይሁን እንጂ፤ (እሱም ተወራለት እንጂ መፍትሔ አላገኘም) የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን መሠረተ እምነቷንና ሥርዓቷን ትውፊቷን ሳይቀር የሚሸረሽሩ ፈርጀ ብዙ ችግሮች፤ዓይነታቸውና ብዛታቸው  ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ከላይ የተመለከትነው የአባቶቻችን መግለጫ፤ "…..ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ተላልፈው ለሞት ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን…" በማለት እውነታውን ፍንትው አድርገው አሳይተውናል፡፡እንደሚታወቀው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ 2ኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ እንደሆኑ፤ይህንን የፓትርያርክነት ሹመት ያገኙት በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት እንደሆነ፤ ከዚያም ንጉሣዊውን ሥርዓተ መንግሥት በጉልበቱ አስወግዶ ሀገሪቱን በተቆጣጠረው ደርግ በተባለው ሃይማኖት የለሽ መንግሥት በግፍ ታፍነው እንደተገደሉ ታሪክ መዝግቦ አስቀምጦታል፡፡ቤተ ክርስቲያንም ምንም ዓይነት የፍትሕ ጥያቄ አለማቅረቧ ብቻ ሳይሆን ፤ቢያንስ አስከሬናቸው በተገቢው ሥፍራ በክብር እንዲያርፍ ሳታደርግ እንዲሁ "እንደ ንጉሡ አጎንብሱ" እንደሚባለው ሆኖ የደርግ መንግሥት እስከሚወድቅ ድረስ የከበረ አስከሬናቸው የነበረበት ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡

Monday, August 13, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሃያ ስድስት

ከክፍል ሃያ አምስት የቀጠለ
የዶግማና የቀኖና ጥሰት በኢ/ኦ/ ተ/ ቤተ ክርስቲያን፤ ክፍል ሁለት
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
       ባለፈው ጽሁፋችን በክፍል ሃያ አምስት ሁለቱን ሲኖዶሶች ወደ አንድነት ለማምጣት የተደረገውን የጋራ ስምምነት መግለጫ አስነብበናችሁ፤ቀጣዩን ክፍል በይደር አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡በገባነው ቃል መሠረት እነሆ ዛሬ ሁለተኛውን ክፍል ይዘን ቀርበናል፡፡
መልካም ንባብ!

Friday, August 10, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሃያ አምስት


የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
ውድ አንባብያን!
       ይህችን "emene tsion" (እናታችን ጽዮን) የተባለችውን የጡመራ መድረክ ከጀመርን ጀምሮ፤“ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” በሚለው ርዕስ አራት ክፍሎችን፣“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” በሚለው ርዕስ ስድስት ክፍሎችን፣“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” በሚለው ርዕስ አስራ አራት ክፍሎችን፤በድምሩ በሃያ አራት ክፍሎች፤ የተለያዩ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳዩች የሚዳስሱ ጽሁፎች እንዳስነበብናችሁ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ "ስለጽዮን ዝም አልልም"በሚለው ዐቢይ ርዕስ ሥር  "የዶግማና የቀኖና ጥሰት"በሚል ንዑስ ርዕስ በወቅታዊው የቤተ ክርስቲያናችንን ሁኔታ ላይ እንወያያለን፡፡
መልካም ንባብ!

Friday, May 11, 2018

ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስራ አራት

ከክፍል አስራ ሦስት የቀጠለ

ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡

የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣እንደምን ሰነበታችሁ?
       በተለያየ አገልግሎት መብዛት ምክንያት በዚች የመወያያ መድረክ ተገቢውን መልእክት ሳናሰተላልፍ በመዘግየታችን አስቀድመን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ለዛሬው ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የፌስ ቡክ ገጻቸው ያስነበቡን ግጥም፤ ሁላችንም እራሳችንን እንድናይና አጥብቀንም እንድንጸልይ የምያበረታታ ስለሆነ ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኃል፡፡
መልካም ንባብ፡፡

Wednesday, August 2, 2017

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስራ ሦስት

ከክፍል አስራ ሁለት የቀጠለ

የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣

     "ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ! ክፉውን ነገር ተጸየፉት…"በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፤ዝግጅቶቹ የእኛ ባይሆኑም፤ የዓላማ አንድነት እስካለን ድረስ፤በተለያዩ የተዋህዶ ልጆች የሚተላለፉትን፤የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ትምህርትና ወቅታዊ መልእክቶች፤ስናካፋላችሁ እንደነበር ታስታውሳላቸሁ፡፡
     በዚሁ መሠረት "ወልድ ዋሕድ "ከተባለው ድረ-ገጽ ላይ ያገኘነውን ጠቃሚ መረጃ እንድትመለከቱት አቅርበንላችኋል፡፡

መልካም ንባብ!

Monday, April 17, 2017

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስራ ሁለት

ከክፍል አስራ አንድ የቀጠለ
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣
     "ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ! ክፉውን ነገር ተጸየፉት…"በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፤ዝግጅቶቹ የእኛ ባይሆኑም፤ የዓላማ አንድነት እስካለን ድረስ፤በተለያዩ የተዋህዶ ልጆች የሚተላለፉትን፤የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ትምህርትና ወቅታዊ መልእክቶች፤ስናካፋላችሁ እንደነበር ታስታውሳላቸሁ፡፡
     ለዛሬው “ፅርፈት ለማን ?”በሚል ርዕስ በ“ካሳሁን ዓለሙ” የተጻፈና በማህበራዊ ድረ ገጽ ለንባብ የበቃውን እጅግ በጣም አስተማሪ የሆነ ጽሁፍ ትማሩበት ዘንድ፤ ጽሁፉ ለንባብ እንዲመች አቀማመጡን ከማስተካከል በስተቀር ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኋል፡፡
መልካም ንባብ!