Monday, August 13, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሃያ ስድስት

ከክፍል ሃያ አምስት የቀጠለ
የዶግማና የቀኖና ጥሰት በኢ/ኦ/ ተ/ ቤተ ክርስቲያን፤ ክፍል ሁለት
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
       ባለፈው ጽሁፋችን በክፍል ሃያ አምስት ሁለቱን ሲኖዶሶች ወደ አንድነት ለማምጣት የተደረገውን የጋራ ስምምነት መግለጫ አስነብበናችሁ፤ቀጣዩን ክፍል በይደር አቆይተነው እንደነበር ይታወሳል፡፡በገባነው ቃል መሠረት እነሆ ዛሬ ሁለተኛውን ክፍል ይዘን ቀርበናል፡፡
መልካም ንባብ!

Friday, August 10, 2018

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል ሃያ አምስት


የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች! እንደምን ሰነበታችሁ?
ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡
ውድ አንባብያን!
       ይህችን "emene tsion" (እናታችን ጽዮን) የተባለችውን የጡመራ መድረክ ከጀመርን ጀምሮ፤“ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ” በሚለው ርዕስ አራት ክፍሎችን፣“ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ” በሚለው ርዕስ ስድስት ክፍሎችን፣“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” በሚለው ርዕስ አስራ አራት ክፍሎችን፤በድምሩ በሃያ አራት ክፍሎች፤ የተለያዩ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳዩች የሚዳስሱ ጽሁፎች እንዳስነበብናችሁ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ "ስለጽዮን ዝም አልልም"በሚለው ዐቢይ ርዕስ ሥር  "የዶግማና የቀኖና ጥሰት"በሚል ንዑስ ርዕስ በወቅታዊው የቤተ ክርስቲያናችንን ሁኔታ ላይ እንወያያለን፡፡
መልካም ንባብ!

Friday, May 11, 2018

ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስራ አራት

ከክፍል አስራ ሦስት የቀጠለ

ለዚች ዕለትና ሰዓት ያደረሰን የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፡፡

የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣እንደምን ሰነበታችሁ?
       በተለያየ አገልግሎት መብዛት ምክንያት በዚች የመወያያ መድረክ ተገቢውን መልእክት ሳናሰተላልፍ በመዘግየታችን አስቀድመን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ለዛሬው ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የፌስ ቡክ ገጻቸው ያስነበቡን ግጥም፤ ሁላችንም እራሳችንን እንድናይና አጥብቀንም እንድንጸልይ የምያበረታታ ስለሆነ ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኃል፡፡
መልካም ንባብ፡፡

Wednesday, August 2, 2017

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስራ ሦስት

ከክፍል አስራ ሁለት የቀጠለ

የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣

     "ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ! ክፉውን ነገር ተጸየፉት…"በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፤ዝግጅቶቹ የእኛ ባይሆኑም፤ የዓላማ አንድነት እስካለን ድረስ፤በተለያዩ የተዋህዶ ልጆች የሚተላለፉትን፤የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ትምህርትና ወቅታዊ መልእክቶች፤ስናካፋላችሁ እንደነበር ታስታውሳላቸሁ፡፡
     በዚሁ መሠረት "ወልድ ዋሕድ "ከተባለው ድረ-ገጽ ላይ ያገኘነውን ጠቃሚ መረጃ እንድትመለከቱት አቅርበንላችኋል፡፡

መልካም ንባብ!

Monday, April 17, 2017

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስራ ሁለት

ከክፍል አስራ አንድ የቀጠለ
የተወደዳችሁ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች፣
     "ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ! ክፉውን ነገር ተጸየፉት…"በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፤ዝግጅቶቹ የእኛ ባይሆኑም፤ የዓላማ አንድነት እስካለን ድረስ፤በተለያዩ የተዋህዶ ልጆች የሚተላለፉትን፤የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ትምህርትና ወቅታዊ መልእክቶች፤ስናካፋላችሁ እንደነበር ታስታውሳላቸሁ፡፡
     ለዛሬው “ፅርፈት ለማን ?”በሚል ርዕስ በ“ካሳሁን ዓለሙ” የተጻፈና በማህበራዊ ድረ ገጽ ለንባብ የበቃውን እጅግ በጣም አስተማሪ የሆነ ጽሁፍ ትማሩበት ዘንድ፤ ጽሁፉ ለንባብ እንዲመች አቀማመጡን ከማስተካከል በስተቀር ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኋል፡፡
መልካም ንባብ!

Sunday, July 31, 2016

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስራ አንድ

ከክፍል አስር የቀጠለ

የተወደዳችሁ አንባብያን!

አሁንም እንደተለመደው "ወልድ ዋሕድ"/www.weldwahed.blogspot.com/ ከተሰኘው ብሎግ ላይ ያገኘነውን ጽሁፍ እነሆ ብለናል፡፡
ሙሉ ዘገባው የ"ወልድ ዋሕድ" ክፍል ሃያ ስድስት ነው፡፡
     ለዛሬው “ጌታሁን ደምፀ” የተባሉት የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ መምህር ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጻፉትንና፤July 29 2016 በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ያስነበኑንን ትምህርት በጣም ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው ለእናንተ ለተዋህዶ ልጆች ማካፈል ስለፈለግን፤ ጽሁፉ ለንባብ እንዲመች ከማስተካከል በስተቀር በሃሳቡ ላይ ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኋል፡፡ይህ ጽሁፍ አጭር ግን ትልቅ ትምህርት ሰጪ በመሆኑና በተለይም በነሐሴ አንድ ቀን የእመቤታችንን የእርገቷን መታሰቢያ ጾም ለመጀመር በተዘጋጀንበት ወቅት የተላለፈ መልእክት በመሆኑ ከወዲሁ እራሳችንን እንድናዘጋጅ የሚያበረታታ ነው፡፡ጾሙን በተገቢው መንገድ ጾመን ከእመቤታችን በረከት እንድናገኝ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን፡፡ አሜን፡፡

Thursday, July 7, 2016

“ ስለጽዮን ዝም አልልም ” ክፍል አስር

ከክፍል ዘጠኝ የቀጠለ
“የቅብአት ምንፍቅና መደበቂያ ካባዎች”

የተወደዳችሁ አንባብያን!

‹‹ስለጽዮን ዝም አልልም ›› በሚለው ዐቢይ ርዕስ ሥር ‹‹"ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ"  በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን›› በሚል በአራት ንዑሳን አርእስት ከፋፍለን ባቀረብነው አጭር ምላሽ፤የተሐድሶዎች የእምነት መግለጫ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን ከገለባ ቀሎ የተገኘ፤ከንቱ የማጭበርበሪያ ሰነድ መሆኑን እንደተገነዘባችሁ እናምናለን፡፡በዚህ አጋጣሚ በነዚሁ አስመሳዮች (የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች) ከንቱ ስብከት ተወናብዳችሁ በየዋህነት እነሱን የምትከተሉ ሁሉ፤እባካችሁ የእግዚአብሔር ቃል መንፈስን ሁሉ መርምሩ እንጂ ዝም ብላችሁ አትመኑ ስለሚል ቆም ብላችሁ እንድታስቡና ወደ እውነተኛይቱ የተዋሕዶ ሃይማኖት እንድተመለሱ አጥብቀን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
አሁንም እንደተለመደው "ወልድ ዋሕድ"/www.weldwahed.blogspot.com/ ከተሰኘው ብሎግ ላይ ያገኘነውን ጽሁፍ እነሆ ብለናል፡፡
ሙሉ ዘገባው የ"ወልድ ዋሕድ" ነው፡፡

     ለዛሬው የምናቀርብላችሁ የ "ቅብአት" እምነትን በተመለከተ “መልካሙ በየነ” የተባሉ የተዋሕዶ ልጅ፤ ከእነዚሁ የ "ቅብአት"እምነት ተከታዮች ከሆኑት በአንዱ ለተዘጋጀ "ወልደ አብ" ለተባለው የክህደት መጸሐፍ የሰጡትን፤ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ያስነበቡንን፤ በአስር ክፍሎች የተዘጋጀ ምላሽ ትልቅ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ስላገኘነው ምንም ሳንጨምርና ሳንቀንስ አቅርበንላችኋል፡፡
ውድ አንባብያን! ምንም ጽሁፉ ረዘም ያለ ቢሆንም፤ ዓላማው እውነቱን ከሐሰት ለመለየትና ሁሉም እራሱን ከስህተት ትምህርት ለመጠበቅ እንዲችል ለማድረግ ስለሆነ፤መምህሩ ለመጻፍ ያልደከሙትን እኛ ለማንበብ መድከም ስለሌለብን፤ በትዕግስትና በጥንቃቄ አንብበን ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንድንወጣ በማለት እያሳሰብን ወደ ቀጣዩ ትምህርታዊ ምላሽ እንመራችኋለን፡፡

መልካም ንባብ!